Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በቃለ መጠይቁ ውስጥ ኤለን ኋይት የተናገረቻቸው ዓረፍተ ነገሮች

    እነዚህን ልምምዶች እየነገርኳችሁ ያለሁት በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለፍን እንድታውቁ ነው፡፡…አንዳንዶች [ከ1844 በኋላ የተነሱ ወግ አጥባቂዎች] «ክብር፣ ክብር፣ ክብር፣ ክብር፣ ክብር፣ ክብር” እያሉ በመዘመር ወደ ላይና ወደ ታች ይደንሱ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እስኪጨርሱ ድረስ ዝም ብዬ እቀመጥና ከጨረሱ በኋላ ተነስቼ እንዲህ እላቸው ነበር፡- «ይህ እግዚአብሔር የሚሰራበት መንገድ አይደለም፡፡ በዚህ መንገድ በአእምሮ ውስጥ ተጽዕኖ አያሳድርም፡፡ ቃሉ የእምነታችን መሠረት ስለሆነ የህዝብን አእምሮ ወደ ቃሉ መምራት አለብን፡፡» {2SM 42.5}Amh2SM 42.5

    በዚያን ጊዜ ልጅ ብሆንም እንኳን እነዚህን እንግዳ ሥራዎች በተመለከተ በተደጋጋሚ ምስክርነቴን ማቅረብ ነበረብኝ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሕዝባችን መካከል ይህን የመሰለ ነገር በድጋሚ እንዳይመጣ እጅግ በጣም ጥንቁቅ መሆን እፈልግ ነበር፡፡ ማንኛውም ዓይነት የወግ አጥባቂነት መገለጥ አእምሮ የእውነት ማስረጃ ከሆነው ከቃሉ እንዲርቅ ያደርጋል፡፡ {2SM 42.6}Amh2SM 42.6

    እናንተ ተለዋዋጭ ያልሆነ መንገድ ልትከተሉ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን በእናንተ ተጽዕኖ ሥር የሚወድቁ ሰዎች እጅግ ዘላቂ ያልሆነ መንገድ ይከተሉና እጃችን ለማያምኑ ሰዎች ስለ መልእክታችንና ስለ ሥራችን ትክክለኛ የሆነ ግምት መስጠት በማይቻል ነገር ይሞላል፡፡ ጽኑ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ይዘን ወደ ሕዝብ መሄድ አለብን፤ ያንን ቃል ሲቀበሉ መንፈስ ቅዱስ ሊመጣ ይችላል፣ ነገር ግን አስቀድሜ እንደተናገርኩ መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው ለሰዎች ፍርድ ራሱን አሳልፎ በሚሰጥበት መንገድ ነው፡፡ በንግግራችን፣ በዝማሬያችን፣ እና በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ እያንዳንዱን እውነተኛ የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ የሚያነሳሳ መረጋጋትን፣ ክብርን እና እግዚአብሔርን መፍራትን ማሳየት አለብን፡፡ {2SM 43.1}Amh2SM 43.1

    እንደ መንፈስ ቅዱስ ሥራ አድርገን የምንቆጥረውን የሆነ ነገር ወደ መካከላችን እንዲመጣ የመፍቀድ የማያቋርጥ አደጋ አለ፣ ነገር ግን እውነታው ሲታይ የወግ አጥባቂነት መንፈስ ፍሬ ነው፡፡ የእውነት ጠላት በስህተት መንገድ እንዲመራን እስከፈቀድንለት ድረስ በልባቸው ታማኝ የሆኑ ልቦችን በሦስተኛው መልአክ መልእክት ለመድረስ ተስፋ ማድረግ አንችልም፡፡ ለእውነት በመታዘዝ መቀደስ አለብን፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ከተገለጸው ጽኑ የእውነት ማስረጃዎች አእምሮን ወደ ሌላ የሚመልሰውን ማንኛውንም ነገር እፈራለሁ፡፡ እፈራዋለሁ፤ እፈራዋለሁ፡፡ ጠላት መጥቶ ሁሉንም ነገር ስርዓት እንዳያሳጣ አእምሮዎቻችንን ከግንዛቤ ወሰን ውስጥ ማድረግ አለብን፡፡ በቀላሉ ወደ አክራሪነት (ወግ አጥባቂነት) እንዲመሩ የሚያደርግ የግርግር ባሕርይ ያላቸው ግለሰቦች አሉ፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎችን ወደ ስህተት የሚመራ ማንኛውም ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲመጣ ብንፈቅድ እነዚህ ስህተቶች ብዙም ሳይቆዩ ወደ ጽንፍ ይሄዱና እነዚህ ሥርዓት የሌላቸው አካሎች ከተከተሉት መንገድ የተነሳ መላው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መጥፎ ስም ይሰጣቸዋል፡፡ {2SM 43.2}Amh2SM 43.2