Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 48—የማንጻት ሥራ ያስፈልጋል

    ውድ ወንድሞቼ ጂ. ኣይ ቡትለር እና ኤስ ኤን ሃስከል፡-

    ለሳምንታት ከሌሊቱ ዘጠኝ ተኩል እስኪሆን ድረስ እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ነበር፡፡ አእምሮዬ እንደ ሕዝብ ስላለንበት ሁኔታ ያሰላስል ነበር፡፡ ከሌሎች የበለጠ ብርሃንና የእውነት እውቀት ስላለን በምድር ላይ ካለው ከማንኛውም ሕዝብ የበለጠ እጅግ መቅደም ነበረብን፡፡ የተሰጠን ታላቅ ብርሃንና የእውነት እውቀት ብርሃንን ለሌሎች እንድናበራ እና እውነትን እናምናለን ከማለት ባለፈ እንድንለማመደው ከፍተኛ ተጠያቂነትን በፊታችን ያስቀምጥልናል፡፡ እውነትን ስንለማመደው የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስን እየተከተልን ነን፡፡ እንደ ሕዝብ ያለማቋረጥ ከፍ እያልን፣ የበለጠ መንፈሳዊ አእምሮ እያጎለበትን ካልሄድን በስተቀር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳንፈጽም በራስ ጽድቅ እንደተሞሉ ፋሪሳውያን እየሆንን ነን፡፡ Amh2SM 376.1

    ከፍተኛ የሆነ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ሊኖረን ይገባል፡፡ በየዕለቱ ሕይወታችን እኛነታችን እጅግ አነስተኛ በሆነ ሁኔታ እና ኢየሱስ ክርስቶስና የእርሱ ጽድቅ በከፍተኛ ደረጃ መታየት አለባቸው፡፡ በዚህ ዓለም ታሪክ ወሳኝ ወቅት ላይ እየኖርን ነን፡፡ የሁሉም ነገር ፍጻሜ ደርሷል፤ ጊዜ በፍጥነት እያለቀ ነው፤ በቅርቡ በሰማይ «ተፈጸመ” ይባላል (ራዕይ 21፡6)፡፡ «ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ እርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ» (ራዕይ 22፡11)፡፡Amh2SM 376.2

    ምስክርነታችን መሰላት አለበት፤ እግዚአብሔርን አጥብቀን እንያዝ፡፡ እርሱ በሰዎች ልብ ላይ እንዲሰራ ከጧቱ በአንድ፣ በሁለት እና በሶስት ሰዓት ላይ መጸለይን አላቋርጥም፡፡ በምድር ላይ እየተካሄደ ባለው ሥራ ላይ ሰማይ በሞላ ስላለው ፍላጎት አስባለሁ፡፡ ልባዊ በሆነ ሕያው እምነት ለሚጸለይ ለእያንዳንዱ ጸሎት ሳይዘገዩ መልስ ለመመለስ የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ ወዲያውኑ ለመፈጸም የተዘጋጁ አገልጋይ መላእክት በዙፋኑ አጠገብ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ስንቶቹ እውነትን እናምናለን የሚሉ ሰዎች እሱን ከሕይወታቸው ለይተውት እየኖሩ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የሚቀድሰውን፣ የሚያነጻውንና መንፈሳዊ የሚያደርገውን ኃይል ወደ ልባቸው አያመጡትም፡፡Amh2SM 377.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents