Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ድነት ከክርስቶስ ጋር መገናኘት ነው

    የተለየ፣ ቅዱስ ሕዝብ ሆነን ሳለ እግዚአብሔር ለእኛ ለገለጠልን ሊነገር ስለማይቻል ፍቅር ስሜት የሌለን ነን ወይ? ድነት ማለት መጠመቅ ማለት አይደለም፣ ስማችን በቤተ ክርስቲያን መዝገብ መጻፍም አይደለም፣ እውነትን መስበክም አይደለም፡፡ ነገር ግን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ሕያው ግንኙነት መፍጠር ነው፤ የልብ መታደስ፣ የክርስቶስን ሥራ በእምነት መሥራትና በትዕግሥት፣ በየዋህነት እና በተስፋ የፍቅር ሥራ መሥራት ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር የተገናኘ እያንዳንዱ ነፍስ በዙሪያው ላሉት ሁሉ ሕያው ሚስዮናዊ ይሆናል፡፡ በቅርብና በሩቅ ላሉት መዳን ይሰራል፡፡ የወገናዊነት ስሜት አይኖረውም፣ እርሱ የመሪነት ሚና የሚጫወትበትን አንድ የሥራ ዘርፍ በመፍጠር ለሥራው ያለው ቅናት ወደ ፍጻሜ እንዲደርስ አያደርግም፡፡ ሁሉንም የሥራ ዘርፎች ጠንካራ ለማድረግ ሁሉም በፍላጎት ይሰራሉ፡፡ የራስ ፍቅርና የራስ ወዳድነት ፍላጎት አይኖርም፡፡ ሥራው አንድ ነው፣ እውነትም አንድ ትልቅ የሆነ ሙሉ ነገር ነው፡፡ Amh2SM 381.3

    «በልቤ ውስጥ ቅንዓት አለን? ምቀኝነትስ በልቤ ውስጥ ቦታ አግኝቷልን?” የሚል ጥያቄ ከእውነተኛ ልብ መጠየቅ አለበት፡፡ እንደዚህ ከሆነ በዚያ ቦታ ክርስቶስ የለም፡፡ «የእግዚአብሔርን ሕግ እወዳለሁን? የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር በልቤ ውስጥ አለን?» ክርስቶስ እንደወደደን እርስ በርሳችን ብንዋደድ ሰላምና እረፍት ላለበት ለተባረከው ሰማይ እየተዘጋጀን ነን፡፡ በዚያ ቦታ የመጀመሪያ ለመሆን፣ የበላይነትን ለመያዝ ትግል የለም፤ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን እንደ ራሳቸው ይወዳሉ፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱን አባል በግል በማነሳሳት ልቦናን በከፈተ እና ለልብ በተናገረ ኖሮ ምንኛ መልካም ነበር፡፡Amh2SM 381.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents