Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 50—የእምነታችን ምሶሶዎች

    በሕይወት በኖርኩባቸው ባለፉት ሃምሳ አመታት ውስጥ ልምድ ማግኘት የምችልባቸው ውድ እድሎች ነበሩኝ፡፡ በመጀመሪያው፣ በሁለተኛውና በሦሥተኛው መላእክት መልእክቶች ላይ ልምድ አግኝቼ ነበር፡፡ መላእክቶቹ በምድር ታሪክ መጨረሻ ላይ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ያለውን የማስጠንቀቂያ መልእክት በማወጅ በሰማይ መካከል እንደሚበሩ ሆነው ተገልጸዋል፡፡ እነዚህ መላእክት ከሰማይ ዩኒቨርስ ጋር በመስማማት እየሰሩ ያሉ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚወክል ምልክት ስለሆነ ማንም ሰው የእነዚህን መላእክት ድምፅ አይሰማም፡፡ ወንዶችና ሴቶች በእግዚአብሔር መንፈስ መረዳትን አግኝተውና በእውነት ተቀድሰው የሦሥቱን መላእክት መልእክት በቅደም ተከተላቸው ያውጃሉ፡፡ Amh2SM 387.1

    በዚህ የከበረ ሥራ ውስጥ እኔም ድርሻዬን ተጫውቻለሁ፡፡ አጠቃላይ የክርስቲያን ልምምዴ ከሱ ጋር የተጠላለፈ ነው፡፡ ከእኔ ልምምድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ልምምድ ያላቸው አሁን በሕይወት ያሉ ሰዎች አሉ፡፡ የወቅቱ እውነት ሲገለጥ ተገንዝበዋል፤ ከታላቁ መሪ፣ የጌታ ሰራዊት አዛዥ ጋር አብረው ተጉዘዋል፡፡Amh2SM 387.2

    በመልእክቶቹ እወጃ እያንዳንዱ የትንቢት መስፈርት ተፈጻሚነትን አግኝቷል፡፡ እነዚህን መልእክቶች በማወጅ ድርሻቸውን ለመወጣት እድል ያገኙት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለውን ልምምድ አግኝተዋል፤ አሁን «ክርስቶስ እዚህ ነው፣” «እውነት እዚህ ነው» የሚሉ ድምፆች በየአቅጣጫው በሚሰሙበት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ጭንቀት ውስጥ ሳለን፣ የብዙዎች ሸክም በዓለም ውስጥ የተለየ ሕዝብ ሆነን ለመቆም ከአብያተ ክርስቲያናትና ከዓለም እንድንወጣ የመራንን የእምነታችንን መሠረት ማናጋት በሆነበት ወቅት፣ ልክ እንደ ዮሐንስ ምስክርነታችን ይተላለፋል፡፡ Amh2SM 387.3

    «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፣ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተም ደግሞ ከእኛ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን” (1 ዮሐ. 1፡ 1-3)፡፡Amh2SM 388.1

    ያየኋቸውን እና የሰማኋቸውን ነገሮች፣ ስለ ሕይወት ቃል እጆቼ የጨበጧቸውን ነገሮች እመሰክራለሁ፡፡ ይህ ምስክርነት የአብና የወልድ ምስክርነት እንደሆነም አውቃለሁ፡፡ እውነት ለሰዎች ሲቀርብ፣ በጽሁፍና በቃል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ እና መልእክቶቹ በቅደም ተከተላቸው ሲተላለፉ የመልእክቶቹን መተላለፍ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳጀበው አይተናል እንመሰክርማለን፡፡ ይህን ሥራ መካድ መንፈስ ቅዱስን መካድ ስለሆነ ጆሮአቸውን ለአሳሳች መናፍስት በመስጠት ከእምነት ከተለዩት ወገኖች ጋር ያስቀምጠናል፡፡ Amh2SM 388.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents