Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 53—ለጄኔራል ኮንፈራንስ የተሰጡ የመጨረሻ መልእክቶች

    «ኤልምሰሀቨን» የጤና ተቋም፣ ካሊፎርኒያ

    ግንቦት 4, 1913 ዓ.ም

    በጄነራል ኮንፍራንስ ተሰብስባችሁ ላላችሁ፣ ሰላም!

    ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡ የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፡፡ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናነናል፣ ስለዚህም እኛ ራሳችን በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን» (2ቆሮ. 1፡ 2-4)፡፡Amh2SM 398.1

    «ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሳቱ ለሚያዞረን ለእኛም በየሥፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምሥጋና ይሁን፤ በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና” (2 ቆሮ. 2፡ 14፣ 15)፡፡Amh2SM 398.2

    «ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፣ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን፡፡ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፡- በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና፡፡ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን” (2 ቆሮ. 4፡ 5-7)፡፡Amh2SM 398.3

    «ስለዚህ አንታክትም፣ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳን የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፡፡ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት ቀላል የሆነው የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፣ የማይታየው ግን የዘላለም ነው» (2 ቆሮ. 4፡ 16-18)፡፡Amh2SM 399.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents