Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዓለምን በሙሉ ይጠራርጋል

    ሰይጣን በሁሉም ዓይነት የአስማት ተጽእኖዎቹ ወደሚሰራበት ጊዜ እየመጣን ነው፣ አሁን በእነዚህ ነገሮች የተማረኩት ወይም ትንሽ እንኳን ፊት የሚሰጡ ሰዎች ሁሉ ያኔ ከሰይጣን ጋር ድርሻቸውን ለመጫወት ተጠራርገው ለመወሰድ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ ክፉ መላእክት በሰዎች ልብ ውስጥ ሁል ጊዜ እየሰሩ ናቸው፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ስር ካልሆነ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር እየሰራ ነው፡፡ ዓለምን ምርኮኛ የሚያደርጉት የሰይጣን የውሸት ተአምራቶች ናቸው፣ እሱ በሰዎች ፊት ከሰማይ እሳት እንዲወርድ ያደርጋል፡፡ ተአምራቶችን ሊሰራ ነው፤ ይህ አስገራሚ የሆነ ተአምራት የሚሰራ ኃይል ዓለምን በሙሉ ሊጠራርግ ነው፡፡ አሁን ገና እየጀመረ ነው፡፡ {2SM 51.2}Amh2SM 51.2

    ሌላ ነገር ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ ጥናዎች የሚፈሱበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ ለይተን የማናውቅበት ምክንያቱ ምንድን ነው? ምክንያቱ የእውነት ብርሃን ልብን ስለማይነካ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር እየተወሰደ ነው፡፡ {2SM 51.3}Amh2SM 51.3

    በምድርና በባሕር መቅሰፍቶችን ትሰማላችሁ፣ እነዚህ መቅሰፍቶች በየጊዜው እየጨመሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው? የሰዎች ሕይወት በእጃቸው ካለ ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ እየተወሰደ ነው፣ ራሳቸውን ለእሱ ቁጥጥር አሳልፈው ስለሰጡ ሰይጣን ሊቆጣጠራቸው እየመጣ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚሉ ሰዎች ራሳቸውን በሰማያዊ መላእክት ጥበቃ ሥር አያደርጉም፣ ሰይጣን አጥፊ ስለሆነ በእነዚያ ሰዎች አማካይነት ስለሚሰራ ስህተቶችን ይፈጽማሉ ይሰክራሉም፣ መሻታቸውን መግዛት ስለማይችሉ ብዙ ጊዜ እነዚህን አሰቃቂ መቅሰፍቶች በላያችን ያመጣሉ፡፡ {2SM 51.4}Amh2SM 51.4

    ማዕበሎቹንና ወጀቦቹን ተመልከቱ፡፡ ሰይጣን በከባቢ አየር ውስጥ እየሰራ ነው፣ ከባቢ አየሩን እየመረዘ ነው፣ እዚህ ሆነን ለሕይወታችን- ለአሁኑና ለዘላለማዊው ሕይወት- በእግዚአብሔር እንደገፋለን፡፡ ባለንበት ቦታ ሆነን ሙሉ በሙሉ ራሳችንን ለእግዚአብሔር ሰጥተን፣ ሙሉ በሙሉ ተለውጠን፣ ሙሉ በሙሉ ተቀድሰን በደንብ መንቃት ያስፈልገናል፡፡ ነገር ግን ሽባ የሆንን መስለን ተቀምጠናል፡፡ የሰማይ አምላክ ሆይ፣ ቀስቅሰን! -- Manuscript 1, 1890. {2SM 52.1}Amh2SM 52.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents