የእውነትና የውሸት ቅልቅል
ሰባት ሰዓት ተኩል እስኪያልፍ ድረስ እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም ነበር፡፡ ጌታ ለወንድም ቲ እንዳስተላልፍ የሰጠኝን መልእክት በአእምሮዬ ይዤ ነበር፡፡ እሱ የያዛቸው ልዩ አመለካከቶች እውነትና ውሸት የተቀላቀለባቸው ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ላለፉት አርባ ዓመታት ሕዝቡን በመራበት ልምምዶች ውስጥ አልፎ ቢሆን ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመጠቀም ዝግጁ ይሆን ነበር፡፡ በትንቢታዊ ታሪክ ውስጥ ያለንን አቋም የሚያሳዩን ትልልቅ የእውነት ምልክቶች እንዳይፈርሱና እውነተኛ ብርሃንን ከማምጣት ይልቅ ውዝግብን በሚያመጡ ንድፈ ሀሳቦች እንዳይተኩ በጥንቃቄ መጠበቅ አለባቸው፡፡ በተደጋጋሚ ይቀርቡ የነበሩ ንድፈ ሀሳቦችን ስጠቅስ ነበር፡፡ እነዚህን ንድፈ ሀሳቦች ያቀርቡ የነበሩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ያቀርቡ ነበር፣ ነገር ግን የተጠቀሟቸው የተሳሳተ ትርጉም በመስጠትና በተሳሳተ መንገድ ነበር፡፡ ትክክል እንደሆኑ የተገመቱት ንድፈ ሀሳቦች ስህተት ነበሩ፣ ሆኖም ብዙዎች ለሰዎች መቅረብ የሚገባቸው ንድፈ ሀሳቦች እንደሆኑ አሰቡ፡፡ የዳንኤልና የዮሐንስ ትንቢቶች በትጋት መጠናት አለባቸው፡፡ {2SM 101.2}Amh2SM 101.2
ልዩ የሆኑ ትንቢቶች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው በመፈጸም ሂደት ላይ ባሉበት መንገድ ላይ እያለፉ ሳሉ የዳንኤልንና የዮሐንስን ትንቢቶች በማጥናት ከእግዚአብሔር ታላቅ ብርሃን የተቀበሉ አሁን በሕይወት ያሉ ሰዎች አሉ፡፡ ለሕዝብ የወቅቱን መልእክት አስተላለፉ፡፡ ጸሐይ በእኩለ-ቀን እንደሚበራ እውነት በግልጽ በራ፡፡ የትንቢትን ቀጥተኛ መሟላት የሚያሳዩ ታሪካዊ ክስተቶች በሰዎች ፊት ቀርበው ነበር፣ ትንቢት ወደዚህ የምድር ታሪክ መዝጊያ የሚመራ የክስተቶች ምሳሌያዊ ዝርዝር ማስረጃ ነው፡፡ ከኃጢአት ሰው አሰራር ጋር የተገናኙ እይታዎች በዚህ የምድር ታሪክ በግልጽ የታዩ የመጨረሻ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ አሁን ሕዝቡ ለዓለም የሚሰጠው የተለየ መልእክት፣ የሶስተኛው መልአክ መልእክት አለው፡፡ በልምምዳቸው በወቅቱ የነበሩና የአንደኛውን፣ የሁለተኛውንና የሶስተኛውን መላእክት መልእክት በማወጅ ድርሻቸውን የተወጡት የእግዚአብሔር ሕዝብ ተግባራዊ እውቀት እንደሌላቸው ሰዎች በስህተት መንገድ በቀላሉ አይመሩም፡፡. . . {2SM 102.1}Amh2SM 102.1
መጽሐፍ ቅዱሳቸውን በማጥናት ታላቅ ብርሃንን እና አዳዲስ ንድፈ ሀሳቦችን እንዳገኙ ያሰቡ ሰዎች አሉ፣ ነገር ግን ትክክል አልነበሩም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በስህተት በመጠቀም ሰዎች ከስህተት ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ፡፡ የተያያዝነው ብርቱ ጦርነት ነው፣ ወደ መጨረሻው ትግል እየተቃረብን ስንሄድ ጦርነቱ እየጠበቀና እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ የማይተኛ ጠላት አለን፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ላለፉት አምሳ አመታት በነበራቸው ትምህርት ላይ የግል ልምምድ በሌላቸው ሰብአዊ አእምሮዎች ውስጥ ያለማቋረጥ እየሰራ ነው፡፡ አንዳንዶች ለእነርሱ ጊዜ የሚሆነውን እውነት ይወስዱና ወደፊት ለሚሆነው ነገር ይጠቀማሉ፡፡ በትንቢት ቅደም ተከተል ውስጥ ከዚህ በፊት ተፈጻሚነት ያገኙት ክስተቶች ወደ ፊት እንደሚፈጸሙ ተደርገው ተወስደዋል፣ ከእነዚህ ንድፈ ሀሳቦች የተነሳ የአንዳንዶች እምነት ተሸርሽሯል፡፡ {2SM 102.2}Amh2SM 102.2
ጌታ ሊሰጠኝ ከወደደው ብርሃን እንደተረዳሁት በእግዚአብሔር ሕዝብ የእምነት ታሪክ ውስጥ የራሳቸው ቦታ ያላቸውንና በወቅቱ የተመደበላቸውን ተግባር የፈጸሙትን እውነቶች በሌሎች ሰዎች ፊት በማቅረብ ተመሳሳይ የሆነ ሥራ የመስራት አደጋ ውስጥ ናችሁ፡፡ እነዚህን በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ያሉ እውነታዎችን እውነት እንደሆኑ ትገነዘባላችሁ፣ ነገር ግን ወደ ፊት እንደሚሆኑ አድርጋችሁ ሥራ ላይ ታውላላችሁ፡፡ እንደ ሕዝብ ዛሬ የሆንነውን እንድንሆን ባደረጉን የክስተቶች ሰንሰለት ውስጥ አሁንም በትክክለኛ ቦታቸው ኃይል አላቸው፣ በዚህ መልክ በስህተት ጨለማ ውስጥ ላሉት መቅረብ አለባቸው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ሰራተኞች ከሶስተኛው መልአክ መልእክት መነሳት ጀምሮ በሥራው ውስጥ ልምድ ካላቸው ወንድሞች ጋር መተባበር አለባቸው፡፡ እነዚህ እየተጓዙ ሳሉ ብርሐንንና እውነትን በመቀበል፣ ተራ በተራ የሚመጣባቸውን ፈተና እየተገሱ፣ በመንገዳቸው ላይ በቀጥታ ተቀምጦ ያለውን መስቀል እያነሱ እና አወጣጡ እንደ ንጋት የተዘጋጀውን ጌታ ለማወቅ ወደ ፊት እየተዘረጉ ደረጃ በደረጃ ተከተሉ፡፡ አንተና ሌሎች ወንድሞቻችን እውነትን መቀበል ያለባችሁ እግዚአብሔር ለትንቢት ተማሪዎቹ እንደሰጠው፣ እውነት ተጨባጭ ነገር እስኪሆንላቸው ድረስ መከራ እየደረሰባቸው፣ እየተፈተኑና እውነተኛነታቸው እየተረጋገጠ ነጥብ በነጥብ ወደ ፊት ሲቀጥሉ ሳለ ትክክለኛ በሆነ ሕያው ልምምድ በተመሩበት ሁኔታ ነው፡፡ እውነት ከድምጾቻቸውና ከብዕሮቻቸው ብሩህ በሆኑና በጋሉ ጮራዎች ወደ ሁሉም የዓለም ክፍሎች ሄዷል፣ እግዚአብሔር በወከላቸው መልእክተኞች አማካይነት በመጣ ጊዜ ለእነርሱ የሚፈትን እውነት የነበረው መልእክት ለታወጀላቸው ሁሉም የሚፈትን እውነት ነው፡፡ {2SM 102.3}Amh2SM 102.3
አሁን በሩቅና በቅርብ ላሉት የእግዚአብሔር ሕዝብ መድረስ ያለበት ማስጠንቀቂያ ሸክም የሶስተኛው መልአክ መልእክት ነው፡፡ ይህን መልእክት ለማስተዋል እየፈለጉ ያሉ ሰዎች መሰረትን የሚሸረሽርና ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች አሁን የሆኑትን እንዲሆኑ ያደረጓቸውን የእምነት ምሶሶዎች የሚያስወግድ የቃል አጠቃቀም ሥራ ላይ እንዲያውሉ ጌታ አይመራቸውም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተገለጸው ትንቢት በሚመራን መስመር ወደ ወደ ፊት በተራመድን ቁጥር ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው እየተገለጡ ያሉ እውነቶች አሁንም እውነት፣ ቅዱስና ዘላለማዊ እውነት ናቸው፡፡ በልምምዳችን ያለፈው ታሪክ ውስጥ በትንቢቶች ውስጥ ያለውን ተከታታይ እውነት በመመልከት ደረጃ በደረጃ ያለፉ ሰዎች እያንዳንዱን የብርሃን ጮራ ለመቀበልና ለመታዘዝ የተዘጋጁ ነበሩ፡፡ እውነትን እንደተደበቀ ሀብት ለማግኘት ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲፈልጉና ሲቆፍሩ ስለነበር እንደምናውቀው መንፈስ ቅዱስ ሲያስተምራቸውና ሲመራቸው ነበር፡፡ ብዙ ንድፈ ሀሳቦች የእውነትን መልክ ይዘው ቀርበው ነበር፣ ነገር ግን የስህተት ትርጉም ከተሰጣቸውና በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ ከዋሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ጋር ስለተቀላቀሉ አደገኛ ወደሆኑ ስህተቶች መሩ፡፡ እያንዳንዱ የእውነት ነጥብ እንዴት እንደተመሰረተና የእግዘአብሔር ቅዱስ መንፈስ ማህተም በላዩ እንዴት እንዳረፈበት እናውቃለን፡፡ «እውነት እዚህ አለ፣” «እውነት አለኝ፤ ተከተሉኝ” የሚሉ ድምፆች ሁል ጊዜ ይሰሙ ነበር፡፡ ነገር ግን «አትከተሏቸው፡፡ እኔ አልላኳቸውም፣ ነገር ግን ይሮጣሉ» የሚሉ ማስጠንቀቂያዎች መጡ፡፡ (ኤርሚያስ 23፡ 21ን ይመልከቱ)፡፡ {2SM 103.1}Amh2SM 103.1
የእግዚአብሔር አመራር በግልጽ የሚታይ ነው፣ ስለ እውነት ምንነት የተሰጡ ራዕዮችም እጅግ አስደናቂ ናቸው፡፡ የሰማይ ጌታ በሆነው እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነጥብ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ተቀምጧል፡፡ ያኔ እውነት የነበረው ዛሬም እውነት ነው፡፡ ነገር ግን «እውነት ይህ ነው፡፡ አዲስ ብርሃን አለኝ” የሚሉ ድምፆች መሰማታቸውን አያቋርጡም፡፡ በትንቢታዊ መስመር የሚታዩ እነዚህ አዳዲስ ብርሃኖች የሚገለጡት ቃሉን በተሳሳተ ሁኔታ በመጠቀምና የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያቆማቸውን መልህቅ በማሳጣት እንዲዋልሉ በማድረግ ነው፡፡ የቃሉ ተማሪዎች እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመራ የገለጠላቸውን እውነቶች ቢቀበሉና ለእነዚህ እውነቶች ተገቢ ቦታ ቢሰጡ፣ ቢያዋህዷቸውና ወደ ተግባራዊ ሕይወታቸው ቢያመጡ ኖሮ ሕያው የብርሃን መተላለፊያ መስመሮች ይሆኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አዳዲስ ንድፈ ሀሳቦችን ለመማር ራሳቸውን ያዘጋጁ ሰዎች የእውነትና የውሸት ቅልቅልን ስለያዙ እነዚህን ነገሮች ታዋቂ ለማድረግ ከሞከሩ በኋላ ጧፋቸውን ከመለኮታዊ መሰዊያ ያልለኮሱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፣ ከዚህ የተነሳ መብራታቸው ጠፍቷል፡፡ --Manuscript 31, 1896. {2SM 104.1}Amh2SM 104.1