Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር ይከበራልን?

    እነዚህ ግንኙነቶች የሚያስደስቱአችሁን እና ለቀልድ፣ ለመቦረቅ፣ ለመብላትና ለመጠጣት እነዚህን ስብሰባዎች የምትወዱ ሰዎችን ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፣ ኢየሱስን ይዛችሁት ትሄዳላችሁ? የጓደኞቻችሁን ነፍስ ለማዳን ፍላጎት አላችሁ? ከእነርሱ ጋር ግንኙነት የመፍጠር ዓላማችሁ ይህ ነው? በእናንተ ውስጥ የክርስቶስ መንፈስ ሕያው ማደሪያ እንዳለ ያያሉ? ይሰማቸዋል? የክርስቶስ ምስክር እንደሆናችሁ፣ ለመልካም ነገር የሚቀና የተለየ ሕዝብ አካል እንደሆናችሁ ይታያል? ሕይወታችሁ «ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ” (ማቴ. 22፡37)፣ እና «ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ” (ማቴ. 19፡19) በሚሉ መለኮታዊ ሕጎች የሚገዛ መሆኑ ይታያል? ለመጥፋት ተዘጋጅተው ላሉ ልቦችና ህሊናዎች መናገር ራሱ ሁሉን ለክርስቶስ አሳልፎ ካልሰጠ ሰው ኃይል በላይ ነው፡፡ ነገር ግን አንደበተ ርቱእነትህና የንግግር ግለትህ የሚያሳዩት ፍላጎትህ ማዕከል ያደረገው የት መሆኑን ነው? {2SM 125.1}Amh2SM 125.1

    በእነዚህ ማህበራት ውስጥ የንግግራቸው ተወዳጅ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ፍላጎትን የሚቀሰቅሱና ደስታን የሚሰጡ ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ስሜትን ማርካት- መብላት፣ መጠጣትና ደስታ መፈለግ አይደለምን? በእነዚህ ስብሰባዎች የክርስቶስ መገኘት የማይታወቅባቸው ናቸው፡፡ እርሱ በፍጹም አይጠቀስም፡፡ የእርሱ ጓደኝነት አይፈለግም፡፡ በእነዚህ አንድነቶች የትና መቼ ነው እግዚአብሔር የሚከበረው? እምኑ ላይ ነው ነፍስ በትንሹም ቢሆን የምትጠቀመው? በጓደኞችህ ላይ ለመልካም ነገር ተጽእኖ የማታሳድር ከሆነ እነርሱ መጥፎ ተጽእኖ እያሳደሩብህ አይደለምን? የሕይወትን መብራት፣ የእግዚአብሔርን ቃል፣ ወደ ጎን በመተው ከእነዚህ ወዳጆች ጋር በነጻነት መቀላቀል እና ወደ እነርሱ ደረጃ መምጣት ይጠቅማልን? ከእውነትና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ከማግኘት በተለየ ነገር የነፍስን ረሃብ ሊያረካ የሚችል ነገር ማግኘት እችላለሁ ብለህ ታስባለህን? የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉ ሰዎች እግዚአብሔር በሀሳባቸው ሁሉ ውስጥ በሌለበት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ምቾት ይሰማቸዋልን? {2SM 126.1}Amh2SM 126.1

    እነዚህ ማህበራት ስብሰባቸውን ያካሄዱ በነበሩበት በዚያው ክፍል ውስጥ ጉባኤው ለአምልኮ ይገናኝ ነበር፡፡ በተቀደሰው የስብከት አገልግሎት ሰዓት የደስታን፣ የመብላትና የመጠጣትን፣ የወይን ጠጅን ከመጠን በላይ የመጠጣትን ሁኔታዎች መርሳት ትችላላችሁን? ይህን ሁሉ እግዚአብሔር በመጽሐፉ ውስጥ መሻትን አለመግዛት እንደሆነ አድርጎ ይጽፈዋል፡፡ ይህ ከዘላለማዊ እውነታዎች ጋር እንዴት አድርጎ ይቀላቀላል? በእነዚህ ለደስታ ተብለው በሚደረጉ ስብሰባዎች ሁሉ በቤልሻጽር ግብዣ ላይ እንደነበረ ሁሉ ምስክር እንዳለ ትረሳላችሁን? ከማይታየው ዓለም የሚለየን መጋረጃ መገለጥ ቢችል ኖሮ የዓለም ተስፋ ማዕከል የሆነውን ክርስቶስን ከሀሳቦቻቸው ባስወጡት በምግብ መደሰቻዎች፣ በሳቅና በቀልድ ላይ ተመስጠው በማየቱ አዳኝ አዝኖ ትመለከቱት ነበር፡፡ {2SM 126.2}Amh2SM 126.2

    እግዚአብሔርን በሚያገለግልና በማያገለግል መካከል መለየት የማይችሉት ሰዎች በእነዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት በሌላቸው ማህበራት ሊማረኩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ማንኛውም እውነተኛ የሆነ ክርስቲያን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር አይችልም፡፡ አስፈላጊ የሆነው የሰማይ አየር በዚያ የለም፡፡ ነፍሱ ባዶነት ይሰማታል፣ ጤዛና ዝናብ እንደሌላቸው እንደ ጊልቦአ ተራራዎች የሚያድሰው የመንፈስ ቅዱስ አለመኖር ይሰማዋል፡፡ {2SM 126.3}Amh2SM 126.3

    ከሁኔታዎች የተነሳ የክርስቶስ ተከታይ አንዳንድ ጊዜ ያልተቀደሱ መደሰቻዎችን ለማየት ይገደድ ይሆናል፣ ነገር ግን የሚያያቸው በሀዘን በተሞላ ልብ ነው፡፡ ቋንቋው የከነዓን ቋንቋ ስላልሆነ የእግዚአብሔር ልጅ እነዚህን የመሳሰሉ ግንኙነቶች (አንድነቶች) በፍጹም አይመርጥም፡፡ ራሱ ወዳልመረጠው ይህን ወደሚመስል ሕብረት የግድ እንዲመጣ ከተደረገ በእግዚአብሔር ይደገፍ፣ ጌታ ይጠብቀዋል፡፡ ነገር ግን ፈተናው የፈለገው ዓይነት ቢሆን በምንም ምክንያት መርሆዎችን መስዋዕት ማድረግ የለበትም፡፡ {2SM 127.1}Amh2SM 127.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents