የእግዚአብሔር መጋቢዎች
ከእነዚህ የምስጢር ማህበራት ጋር ራሳችሁን ያገናኛችሁ ሰዎች ስብርብሩ በሚወጣ በትር እየተማማናችሁ ነው፤ የእርሱን ፈቃድ ለማወቅና የእርሱን መንገድ ለመከተል ተግቶ በመፈለግ በእሥራኤል ጌታ በእግዚአብሔር አትተማመኑም፡፡ በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ገንዘባችሁን ስታፈሱ ለወደፊቱ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ችላ ተብሎ ለእነርሱ ጊዜአችሁን፣ ሀሳባችሁን ጉልበታችሁንና ገንዘባችሁን ሰጥታችኋል፡፡ በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የተከፈለ እያንዳንዱ ዶላር በባህር ውስጥ እንደሰመጣ ያህል በእውነት በእግዚአብሔር ሥራ ላይ እንዳይውል ተከልክሏል፡፡ ነገር ግን ይህ ገንዘብ እንደ እናንተ ላሉ ሰዎች ድነት እንዲውል በአገልግሎቱ ውስጥ እንድትጠቀሙ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ አልነበረምን? እግዚአብሔርን በማያከብርበትና ሰዎችን በማይጠቅምበት ቦታ ሥራ ላይ በማዋል የጌታውን መክሊት ወስዶ በአፈር ውስጥ የቀበረውን የሀኬተኛ ባሪያን ኃጢአት እየደገማችሁ ነው፡፡ {2SM 132.3}Amh2SM 132.3
ጌታ ታማኝ ላልነበረው ባሪያ ብዙ ገንዘብ ሳይሆን አንድ መክሊት ብቻ ነበር የሰጠው፡፡ ሰውዬው ያንኑ አንድ መክሊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም አላዋለውም፤ ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ፣ ካልበተነበት የሚሰበስብ ጨካኝ ጌታ እንደሆነ በመናገር በአፈር ውስጥ ቀብሮ ደበቀው፡፡ ይህ ሰው ያሳየው ራስ ወዳድነትና እግዚአብሔር የማይገባውን ነገር እንደሚጠይቅ አድርጎ ያቀረበው ቅሬታ እግዚአብሔርን ወይም እርሱ የላከውን ኢየሱስን አለማወቁን አሳየ፡፡ እርሱ የነበረው እያንዳንዱ ነገር ለእግዚአብሔር እንዲጠቀም የተሰጠው የእግዚአብሔር የራሱ ንብረት ነው፡፡ ይህ ሰው፣ «ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ” (ማቴ. 25፡25) ሲል መክሊቱ የእግዚአብሔር እንደነበረ አምኖ ተቀብሏል፡፡ {2SM 133.1}Amh2SM 133.1
ጌታ ምን ይላል? «ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?” (ማቴ. 25፡26)፡፡ እዚህ ላይ የባሪያውን ቃላት ትክክለኛነት በመቀበል ሳይሆን በራሱ አገላለጽ እንኳን ባሪያው ማድረግ የነበረበትን በመግለጽ ቃላቱን ይደግማል፡፡ ጌታም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲህ ይላል፡- «የሰጠሁህን ገንዘብ ነግደህ ለማትረፍና በምድር ላይ ክብሬን ለመጨመር ምንም ጥረት አላደረግክም፡፡” «ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል» (ማቴ. 25፡27-30)፡፡ ለእያንዳንዱ የእውነት ብርሃን ለመጣለት ነፍስ ይህ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ {2SM 133.2}Amh2SM 133.2
ለወደፊቱ ሕይወት ገጣሚዎች መሆናችንን ለመወሰን በዚህ ዓለም ላይ እግዚአብሔር በሙከራ ላይ እንዳስቀመጠን በፍጹም መርሳት የለብንም፡፡ ባሕርዩ በራስ ወዳድነት መጥፎ ቀለም የተበከለ ማንም ቢሆን ሰማይ መግባት አይችልም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እዚህ ጊዜያዊ ሀብት በመስጠት ይፈትነናል፣ የዚህ ሀብት አጠቃቀማችን ዘላለማዊ ሀብት አደራ ሊሰጠን እንደሚችል ወይም እንደማይችል ያሳያል፡፡ ከሰማይ ጋር መስማማት እና እዚያ ለመግባት ገጣሚዎች መሆን የምንችለው ራስን መስዋዕት የሚያደርግ የክርስቶስ ሕይወት በእኛ ሕይወት ሲንጸባረቅ ብቻ ነው፡፡ {2SM 134.1}Amh2SM 134.1