Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከእግዚአብሔር ጋር ትተባበራላችሁን?

    በሰዎች አእምሮዎች ውስጥ በራሳቸው ፈቃድ የተፈጸመ እውርነት አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ «በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል” (ማቴ. 13፡15)፡፡ ለሰዎች ድነት የሚያስፈልገው የእግዚአብሔር ሥራ በዓለማችን ውስጥ ወደ ፊት መቀጠል ያለበት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሥራ ነው፤ የብዙዎች ፍላጎት ግን ከክርስቶስ ታማኝ ወታደሮች ጋር ከመሆን ይልቅ ከጠላት ወገን ስለሆነ ይህን አያዩም፡፡ ሰብዓዊው ከመለኮታዊው ወኪሎች ጋር የመተባበርን አስፈላጊነት አያዩም፡፡ ጌታ እንዲህ በማለት ጠርቶናል፡- «በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና” ፊሊ. 2፡12፣13)፡፡ በሕይወት እቅዶችና ዓላማዎች ሁሉ ሊመራን እግዚአብሔር የገለጠልን እቅድ ይህ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች፡- «መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” (ማቴ. 6፡10) ብለው እየጸለዩ ሳለ እግዚአብሔር መንግሥቱን የሚመሰርትበትን ዋና መንገድ አልቀበል ይላሉ፡፡ {2SM 135.3}Amh2SM 135.3

    ክርስቶስን ለማግኘት ሲሉ ሁሉንም ነገር እንደ ጉዳት ለመቁጠር ፈቃደኛ ሲሆኑ ነገሮችን እንዳሉ ለማየት ዓይኖቻቸው ይገለጣሉ፡፡ ከዚያ በኋላ በምድር ላይ ካሉ ከሚስቡ ነገሮች ወደ ሰማያዊ ነገሮች ይመለሳሉ፡፡ ከዚያም አሁን ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጣቸውን ዓለማዊና ራስ ወዳድነት ያለባቸውን ደስታዎች ትክክለኛ የሆነ ባሕርይ ይመለከታሉ፣ አሁን እንደ ውድ ነገር አድርገው የያዙአቸውን ነገሮች ይተዋሉ፡፡ {2SM 136.1}Amh2SM 136.1

    ለሟች ሰው ተሰጥቶ ከሚታውቀው ነገር ሁሉ እጅግ ቅዱስ በሆነው እውነት እንደምታምኑ የምትናገሩ ሰዎችን ሰማይ በሞላ እየተመለከታችሁ ነው፡፡ ለነፍሳት ድነት ስትሰሩ ከእናንተ ጋር ለመተባበር መላእክት በታላቅ ናፍቆት እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከሚረገጡበትና እግዚአብሔር ከማይከበርበት ሕብረት ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለመጠበቅ ይህንን ሰማያዊ ሕብረት እምቢ ትላላችሁን? እውነትን በማስፋፋት ረገድ ከእናንተ መካከል አንዳንዶቻችሁ እንደምታደርጉት ሌሎችም አነስተኛ ፍላጎት አሳይተው ቢሆን ኖሮ እውነት ወደ እናንተ እንዴት ሆኖ መምጣት ይችል ነበር? የእግዚአብሔርን ሥራ በትክክለኛ መሰረት ላይ ለመመስረትና እውነት ሊጠፉ የተዘጋጁ ነፍሳት ወዳሉባቸው አዳዲስ መስኮች እንዲወሰድ የእኛን እርደታ ይጠይቃል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆናችሁ የምትናገሩ ሰዎች በዚህ ሥራ ውስጥ ለመርዳት እምቢ ማለት ትችላላችሁን? ምድራዊ ትርፍን ለመቀበል ሀብታችሁን ከሰማያዊ መዝገብ በመከልከል የእርሱ ሥራ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ችላ እንዲባል ትፈቅዳላችሁን? እውነትን እናምናለን የሚሉ ሰዎች ሁሉ ልብ ሳይከፋፈል ለእግዚአብሔር ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ነፍሳትን በማዳን ሥራ ሊፈጸም የሚችላውን ነገር ማሰብ አሳዛኝ ነው፡፡ ሥራው በቸልተኝነት ተሰርቷል፡፡ እኔነት በክርስቶስ ተደብቆ ቢሆን ኖሮ ኃጢአተኞች ትጋትና ጥበብ ባለባቸው መንገዶች ለእውነት በመሸነፍ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ይተባበሩ ነበር፡፡ {2SM 136.2}Amh2SM 136.2

    ለሰረኸው ሥራ ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥበት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት አሁን ለቃሉ ጆሮህን እንድትሰጥ አደፋፍርሃለሁ፣ በምስጢር ማህበራት ሳይሆን «ለእናንተ በሰማያት መዝገብ ሰብስቡ» (ማቴ. 6፡20፤ ሉቃስ 12፡33)፡፡ በዪኒቨርስ ውስጥ አንድ ባለቤት ብቻ መኖሩንና እያንዳንዱ ሰው ከጊዜው፣ ከችሎታው፣ ከሀብቱ ጋር ለነፍሱ ቤዛ ለከፈለው ለአንዱ ንብረት መሆኑን ይገንዘብ፡፡ እግዚአብሔር የማያቋርጥ አገልግሎትንና ከሁሉ የበለጠ ፍቅርን እንዲሰጡት የተቀደሰ መብት አለው፡፡ መስፈርትህ መሆን ያለበት የአንተ ደስታ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሀብትን በአነስተኛ ፍጥነት እያከማቸህ ቢሆንም በሰማይ ሀብት እየሰበሰብክ ነህ፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊነቱን ለመጠበቅ ቁርጥ ውሳኔ ያደረገ ማን ነው? ኃይልን በመቆጠብ ክርስቲያናዊ ግለትን የሚገልጥ ልምምድ የሚያጎለብት ማን ነው? ራስን ለማገልገል ያለውን ሀብት በመጨበጥ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ በመስራት እንደ ኢየሱስ ተስፋ የማይቆርጥ ማን ነው? {2SM 137.1}Amh2SM 137.1

    የዘላለም ሕይወትን ዘውድ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ያሉ ሁሉ ጌታቸው እንደተፈተነ እነርሱም ይፈተናሉ፡፡ እሱ ለሰይጣን ቢታዘዝ ኖሮ የዓለምን መንግሥታት ሊሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር፡፡ በቀረበለት ፈተና ክርስቶስ ተሸንፎ ቢሆን ኖሮ ዓለም ለዘላለም ለክፉው አልፎ ይሰጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይድረሰው፣ መለኮታዊነቱ በሰብዓዊነት ውስጥ አበራ፡፡ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በኢየሱስ ስምና ብርታት ሊያደርግ የሚችለውን ነገር አደረገ፡፡ እንዲህ አለ፣ «ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል” (ማቴ. 4፡10)፡፡ አንተም ፈተናን የምትጋፈጠው በዚህ መልክ ከሆነ ክርስቶስን ትቶት እንደሄደ ሁሉ አንተንም ትቶ ይሄዳል፣ መላእክት ክርስቶስን እንዳገለገሉት ሁሉ አንተንም ያገለግሉሃል፡፡ {2SM 137.2}Amh2SM 137.2

    ከአለም ጋር ሕብረት በመፍጠር ስለሚገኙት ታላላቅ ጥቅሞች ስላሰቡና ስላወሩ ሰዎች እግዚአብሔር በነቢዩ ሚልክያስ አማካይነት እንዲህ ይላል፡- {2SM 137.3}Amh2SM 137.3

    «ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል እግዚአብሔር፦ እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል። እናንተም፡- እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል? አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል” (ሚል. 3፡13-15)፡፡ {2SM 137.4}Amh2SM 137.4

    ቃላቱ ባይነገሩም እነዚህ ነገሮች የብዙዎች አስተሳሰብ ነው፡፡ {2SM 138.1}Amh2SM 138.1

    «የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።» «እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ። እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” (ሚል. 3፡16-4፡1)፡፡ {2SM 138.2}Amh2SM 138.2

    በዓለም ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳላቸው ተደርገው የተቆጠሩ ሰዎች እዚህ አሉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች እርሱን ስላከበሩት እንደተከበሩ ሆነው ተለይተው የሚታዩበት ጊዜ ይመጣል፡፡ {2SM 138.3}Amh2SM 138.3

    «የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል» (1ዮሐ. 3፡1-3)፡፡ {2SM 138.4}Amh2SM 138.4

    የተሻለው መንገድ

    ጊዜያዊ ክብር፣ ሃብትና ሥልጣን የዚህ ዓለም ሰዎች ሊያገኙአቸው የሚፈልጓቸው ታላላቅ ነገሮች ሲሆኑ ከዚህ የበለጠ ዋጋ ስላለው ለማግኘት መናፈቅ ያለብንን ነገር ጌታ ያመለክተናል፡፡ {2SM 138.5}Amh2SM 138.5

    «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ ነገር ግን የሚመካው፡- ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ጌታ፡- እነሆ የተገረዙትን ባልተገረዙት የምቀጣበት ዘመን ይመጣል ይላል” (ኤር. 9፡ 23-25)፡፡ {2SM 139.1}Amh2SM 139.1

    «በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው። እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ” (1ጴጥ. 2፡6-9)፡፡ {2SM 139.2}Amh2SM 139.2

    «ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ። እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ። ዳሩ ግን፡- እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ። ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ» (1ጴጥ. 1፡13-19)፡፡ --Pamphlet published in 1893, Should Christians Be Members of Secret Societies? {2SM 139.3}Amh2SM 139.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents