Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 16—የክርስቶስ ሕይወት ሥራና የእኛ

    [Appeared In Notebook Leaflets, Methods, NO. 6.]

    በዚህች ምድር ላይ በየዋህነትና ራስን ዝቅ በማድረግ «መልካም ነገርን በማድረግ” (የሐዋ.10፡38) ስለተመላለሰው እና ያዘኑትን በማጽናናት፣ ችግረኞችን በመርዳት፣ አንገታቸውን የደፉትን በማቃናት ሕይወቱን በፍቅር አገልግሎት ስለጨረሰው እናነባለን፡፡ እንደ ተጓዥ መንገደኛ ጓደኞቹ ቸርነት በማድረግ ካስጠጉት በስተቀር በዚህች ዓለም ላይ ቤት አልነበረውም፡፡ ነገር ግን እርሱ የተገኘበት ቦታ አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሰማይ ሆኖላቸው ነበር፡፡ በየቀኑ ፈተናና ችግርን ይጋፈጥ ነበር፣ ነገር ግን በፈተና ወድቆ ወይም ተስፋ ቆርጦ አያውቅም ነበር፡፡ በሕግ ተላላፊዎች ተከቦ ነበር፣ ነገር ግን የአባቱን ትዕዛዛት ይጠብቅ ነበር፡፡ ሁልጊዜ ትዕግሥተኛና ደስተኛ ነበር፣ በስቃይ ውስጥ የነበሩት የሕይወት፣ የሰላምና የጤና መልእክተኛ አድርገው በመመልከት ያመሰግኑት ነበር፡፡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ምን እንደሚያስፈልጋቸው በመመልከት ለሁሉም እንደሚከተለው ግብዣውን ያቀርብላቸዋል፣ «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴ. 11፡28-30)፡፡ {2SM 154.1}Amh2SM 154.1

    ክርስቶስ በሕይወት ሥራው እንዴት ያለ ምሳሌ ነው የተወልን! ከልጆቹ መካከል እርሱ እንዳደረገ ለእግዚአብሔር ክብር የሚኖር ማን ነው? እርሱ የዓለም ብርሃን ነው፣ ለጌታ በተሳካ ሁኔታ የሚሰራ ሰው ጧፉን ከእርሱ መለኮታዊ ሕይወት መለኮስ አለበት፡፡ {2SM 154.2}Amh2SM 154.2

    ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፣ «እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም» (ማቴ. 5፡13)፡፡ በሕይወት ሥራችን የክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል ምንኛ ጥንቁቆች መሆን አለብን፡፡ ይህን ካላደረግን በስተቀር ለዓለም ምንም አንጠቅምም፣ ጣዕሙን ያጣ ጨው ነን፡፡. . . {2SM 155.1}Amh2SM 155.1

    እግዚአብሔር በሥራው ውስጥ የተለያዩ ዓይነት መክሊቶችን ይጠቀማል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ሥራ በተለያዩ መሳሪያዎች አማካይነት ያከናውናል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ራሱን ብቻ መምህር ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር እየሰራ አይደለም፡፡ «እኔ በማገለግለው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእኔ ተጽእኖ ብቻ እንዲነገር እፈልጋለሁ» የሚል ማንም ቢሆን ብርሃኑ ለጌታ እንዲበራ እየፈቀደ አይደለም፡፡ አብረዋቸው ለሚሰሩ ሰዎች ትህትና የማያሳዩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ጉዳያቸውን ይጨርሳሉ፡፡ ሕዝቡ እንዲያገኝ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ብርሃን በተጽእኖአቸው እንዳያገኙ ያደርጋሉ፡፡ እግዚአብሔር ማረጋገጫ የማይሰጠውን መንፈስ ይገልጣሉ፡፡ {2SM 155.2}Amh2SM 155.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents