ምዕራፍ 19—ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባራዊ ትምህርት
ለብዙዎች የሰለሞን ክህደት ጅምሮች ከትክክለኛ መርህ ትንሽ ማፈንገጥ እንደሆነ ሊመስል ይችላል፡፡ ከጣዖት አምላኪ ሴቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር ብቻውን ለውድቀቱ ምክንያት አይደለም፡፡ ሰለሞንን ወደ አባካኝነትና ጭካኔ ወደተሞላበት ጭቆና ከመሩት ግንባር ቀደም ምክንያቶች መካከል አንዱ የመመኘት መንፈስን በማሳደግና በመንከባከብ የወሰደው እርምጃ ነበር፡፡ {2SM 173.1}Amh2SM 173.1
በጥንቱ የእሥራኤል ዘመን ሙሴ በሲና ተራራ ግርጌ ለሕዝቡ «በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ” (ዘጸ. 25፡8) የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝን በነገረ ጊዜ የእሥራኤላውያን መልስ ትክክለኛ በሆኑ ስጦታዎች የታጀበ ነበር፡፡ «ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ” (ዘጸ. 35፡21)፡፡ ለቤተ መቅደስ ግንባታ ታላላቅና ወድ ዝግጅቶች አስፈላጊ ነበሩ፤ እጅግ የከበሩና ውድ ነገሮች በብዛት ይፈለጉ ነበር፤ ሆኖም እግዚአብሔር የተቀበለው የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ነበር፡፡ «ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፣ በገዛ እጁ ሊሰጠኝ በልቡ ከሚያምረው ሰው ሁሉ መባ ተቀበሉ» (ዘጸ. 25፡2)፣ የሚለው ሙሴ ለጉባኤው ደጋግሞ የነገረው መለኮታዊ ትዕዛዝ ነበር፡፡ ለልዑል የመኖሪያ ቦታን ለማዘጋጀት የመጀመሪያው መስፈርት ለእግዚአብሔር መሰጠትና የመስዋዕትነት መንፈስ ነበር፡፡ {2SM 173.2}Amh2SM 173.2
ዳዊት ለሰለሞን ቤተ መቅደስ የመስራትን ኃላፊነት ባሰተላለፈ ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ ራስን መስዋዕት የማድረግ ጥሪ ተደርጎ ነበር፡፡ የልግስና ሥጦታቸውን ይዘው የመጡትን ሕዝብ ዳዊት እንዲህ በማለት ጠየቀ፣ «ዛሬ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚቀድስ ማነው? (1ኛ ዜና 29፡5)፡፡ የቤተ መቅደሱን ግንባታ ማካሄድ በነበረባቸው ሰዎች አእምሮ ይህ ጥሪ ሁልጊዜ መጠበቅ ነበረበት፡፡ {2SM 174.1}Amh2SM 174.1
የምድረ በዳውን ድንኳን ለመገንባት ለተመረጡት ሰዎች እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ ብልሃትና ጥበብ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ «ሙሴም የእስራኤልን ልጆች አላቸው። እዩ፥ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሆርን የልጅ ልጅ፥ የኡሪን ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላበት፤ የጥበብን ሥራ ያስተውል ዘንድ፥ በወርቅና በብር በናስም ይሠራ ዘንድ፥ በፈርጥ የሚሆነውን የዕንቍ ድንጋይ ይቀርጽ ዘንድ፥ እንጨቱንም ይጠርብ ዘንድ፥ የብልሃት ሥራውንም ሁሉ ይሠራ ዘንድ። እርሱና የዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ያስተምሩ ዘንድ በልባቸው አሳደረባቸው። በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ በቀይም ግምጃ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ» (ዘጸ. 35፡30-35)፡፡ «ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ባስልኤልና ኤልያብ በልባቸው ጥበበኞችም ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነገር ሁሉ አደረጉ» (ዘጸ. 36፡1)፡፡ እግዚአብሔር ራሱ ከመረጣቸው ሰራተኞች ጋር ሰማያዊ ኃይሎች ተባብረዋል፡፡ {2SM 174.2}Amh2SM 174.2
የእነዚህ ሰዎች ተወላጆች ለቅድመ አያቶቻቸው የተሰጠውን ሙያ በከፍተኛ ደረጃ ወርሰዋል፡፡ በይሁዳና በዳን ጎሳዎች ውስጥ በእደ ጥበብ ሥራ በተለየ ሁኔታ ብልሃተኞች የሆኑ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለጊዜው እነዚህ ሰዎች ትሁታንና ራስ ወዳድ ሳይሆኑ ቆዩ፤ ነገር ግን ቀስ በቀስ፣ ሳይታይ፣ በእግዚአብሔርና በእውነቱ ላይ ያላቸውን መሰረት ለቀቁ፡፡ ብልጫ ካለው ሙያቸው የተነሳ ከፍተኛ ደሞዝ መጠየቅ ጀመሩ፡፡ በአንዳንድ አጋጣሚዎች የጠየቁት ተሰጥቷቸዋል፣ ነገር ግን እነዚያ ከፍተኛ ደሞዝ የሚጠይቁት በዙሪያቸው ባሉ አገሮች ሥራ አገኙ፡፡ ዝነኛ በነበሩ ቅድመ አያቶቻቸው ልብ ውስጥ ሞልቶ በነበረው ራስ ወዳድነት የሌለው የከበረ መንፈስ ፋንታ የበለጠውን ለመጨበጥ እየፈለጉ የስስትን መንፈስ ተንከባከቡ፡፡ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሙያ የአህዛብ ነገሥታትን በማገልገል ፈጣሪያቸውን አዋረዱ፡፡ {2SM 174.3}Amh2SM 174.3