Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 21—በተቋሞቻችን ውስጥ ያሉ ሰራተኞች

    ከሁሉ የተሻሉ መክሊቶችን ማግኘት

    በተለያዩ ተቋሞቻችንና በሥራችን ውስጥ ባሉ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ለመስራት ከሁሉ የተሻለውን መክሊት የማግኘትን አስፈላጊነት በተመለከተ ለወንድሞቻችን ምስክርነት እንዳስተላልፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ የጌታ መንፈስ እየገፋፋኝ መሆኑ ተሰምቶኛል፡፡ ስለዚህ ከሥራው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እግዚአብሔር ሊያስተምራቸው የሚችላቸውና ልክ ዳንኤልን በጥበብና በማስተዋል እንዳከበረው ሊያከብራቸው የሚችላቸው የሰለጠኑ ወንዶችና ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚያስቡ፣ የእግዚአብሔር አሻራ ያለባቸው፣ በቅድስና፣ በከበረ ግብረገብ እና በሚሰሩት ሥራ ከሌሎች በልጠው የሚገኙ ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡ የሚያድጉ ሰዎች ቢሆኑ ኖሮ፣ የሚያገናዝብ አእምሮና የተቀደሰ እውቀት ቢኖራቸው ኖሮ፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚሰሙ እና ከሰማይ የሚመጣውን እያንዳንዱን የብርሃን ጨረር ለመያዝ የሚሹ ቢሆኑ ኖሮ እንደ ፀሐይ ጨረር የማይዛነፍ መንገድ የሚከተሉ ይሆኑና በጥበብ እና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘት ያድጉ ነበር፡፡. . .Amh2SM 190.1

    ከተቋሞቻችን ጋር በተገናኘ ሁኔታ በመሪነት ቦታ የተቀመጡ ሰዎች የተማሩ ሰዎችን ማክበር እንዲችሉ በቂ የሆነ የአእምሮ ስፋት ያላቸውና ለሚሸከሙአቸው ኃላፊነቶች ተመጣጣኝ የሆነ ካሣ የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ተሰማርተው የሚሰሩ ሰዎች ለሚከፈላቸው ደሞዝ ብቻ የሚሰሩ መሆን የለባቸውም፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን ለማስከበር፣ ሥራውን ወደ ፊት ለማስቀጠል እና የማይጠፋ ሀብት ለማግኘት የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡ ማሰብንና ልፋትን የሚጠይቅን ሥራ በረቀቀ እና በተሟላ ሁኔታ መስራት የሚችሉ ሰዎች አነስተኛ ሙያ ካላቸው ሰራተኞች የበለጠ ዋጋ ሊከፈላቸው አይገባም ብለን መጠበቅ የለብንም፡፡ ለመክሊት ትክክለኛ የሆነ ግምት መሰጠት አለበት፡፡ እውነተኛ ሥራንና የአእምሮ ችሎታን ማድነቅ የማይችሉ ሰዎች ተጽእኖአቸው ሥራውን ወደማሰር፣ በእድገቱ ላይ እንቅፋት ወደማስቀመጥ እና ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ወደማውረድ ስለሚያዘነብል በሥራ አስኪያጅነት ቦታ መቀመጥ የለባቸውም፡፡ Amh2SM 190.2

    ተቋሞቻችን እግዚአብሔር እንዲሆኑ እንዳቀደው ሀብታሞች ቢሆኑ ኖሮ ካልተዳከመ ቅናትና ጥበብ ካለበት ሥራ ጋር ተደባልቆ የበለጠ ማሰብና ልባዊ የሆነ ጸሎት መኖር ነበረበት፡፡ እነዚህን ሰራተኞች ከሥራው ጋር ማገናኘት ብዙ ወጪን ማውጣት ሊጠይቅ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከተቻለ በሁሉም ነገር ላይ ቁጠባ መለማመድ አስፈላጊ ቢሆንም ወጪን ለመቀነስ ሲባል ሥራቸው ከደሞዛቸው ርካሽነት ጋር በሚነጻጸር መልኩ በርካሽ የሚሰሩ ሰዎችን መቅጠር በመጨረሻ የራሳቸውን ጥፋት ያመጣል፡፡ የሥራው እድገትም ወደ ኋላ ይሄዳል፣ ሥራውም ይናቃል፡፡--Letter 63, 1886.Amh2SM 191.1