Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የሠለጠኑ ሠራተኞች አስፈላጊነት

  በዕድሜ የገፉ ሰዎች የሚያካሂዱትን ሥራ ወጣቶች መረከብ አለባቸው፡፡ ለወጣቶች መሠረት ያለው ትምህርት አለመስጠት ታላቅ ጥፋት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እየገሠገሠ ሲሄድ እኛም ወደፊት ሂድ የሚለውን ትዕዛዝ መከተል አለብን፡፡GWAmh 42.6

  ከጊዜ ጋር የማይነፍሱ ጽኑ ወጣቶች በጥብቅ ይፈለጋሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚራመዱ፤ተግተው ሳይታክቱ የሚጸልዩ፣፤ የቻሉትን ያህል ብርሃን ለመቀበል የሚጥሩ ወጣቶች ይፈለጋሉ፡፡GWAmh 43.1

  የእግዚአብሔር ሠራተኛ ከአምላክ የተሰጠውን የአእምሮና የግብረገብ እስከመጨረሻው ከፍተኛ ደረጃ ማዳበር አለበት፡፡ ክንውንነት የሚያገኘው ግን በዕውቀቱ ብዛት ሳይሆን ሰሥራው ባደረበት ናፍቆት መጠን መሆኑን ምን ጊዜም ማወቅ አለበት:: አርግጥ ጥሩ ትምህርት አግኝቶ ምሁር ሆኖ መገኘት መልካም ነው:: ግን አምላክ ከሰው ጋር ካልተባበረ መልካም ውጤት ማግኘት ዘበት ነው፡፡GWAmh 43.2

  እግዚአብሔር ሥራ ሲኖረው ሰው መርጦ ሳይሆን ሁሉን ይጠራል፡፡ ዛሬም በአካል የዳበሩትን በአእምሮ የበሰሉትን ወጣቶች ይፈልጋል፡፡ በሙሉ አቅማቸው የሰይጣንን ክፉ ሥራዎች እንዲቋቋሙ ይጠባበቅባቸዋል፡፡ ግን የሚያስፈልገውን ዝግጅት ማግኘት አለባቸው፡፡ አንዳንድ ወጣቶች የማይገጥማቸውን ሥራ ሊሠሩ ይሰለፋሉ፡፡ ከማስተማር በፊት መማር ማስፈለጉን ይዘነጋሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በዝቅተኛ ትምህርት ከፍተኛ ክንውን ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡GWAmh 43.3

  እነዚያ ሰዎች የተከናወነላቸው በሙሉ ልባቸው ስለጣሩ ይሆናል፡፡ በዚያ ላይ ለሥራው በሚገባ ሰልጥነው ቢሆን ኖሮ እንዴት አጽፍ ድርብ ወጤት ባገኘን ነበር!GWAmh 43.4

  የአግዚአብሐር ሥራ ሠርተው የሚያደሙ (የሚጠቅመን ሰዎች ይፈለጋል፡፡ መማርና መሠልጠን ለሥራው ከሚያስፈልጉት ዋና ነገሮች መካከል ናቸው፡፡ የመጨረሻውን የምህረት ቃል ለዓለም ለማዳረስ ብዙ ዝግጅት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ ይህ ዝግጅት ስብከትን በማዳመጥ ብቻ አይገኝም፡፡ በትምህርት ቤታችን የሚማሩት ወጣቶች የቀንበር ተሸካሚነት ግዴታ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ከታወቁ መምህራን ጠቃሚ ትምህርት መቀበል አለባቸው፡፡ የጥናት ጊዜአቸውን በሚገባ ተጠቅመውበት የተማሩትን ዕውቀት ከሥራ ላይ ማዋል አለባቸው፡፡ በማንኛውም የሥራ መስክ ብቁ ሆኖ ለመገኘት ጠንክሮ ማጥናትና መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ሳያቋርጡ በመኮትኮት የተሰጠንን መክሊት ልናሳድግ ይገባናል፡፡GWAmh 43.5

  ወጣቶቻችን የበሰለ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ሳይኖራቸው አስተምሩ ማለት ከጉዳት ላይ መጣል ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹ በሥራው ላይ የሚገኙ ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸው ጥሬ ነው፡፡ በሌላም በኩል ቢሆን ብዙ ጉድለት አለባቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባቸው ሳይቀር በማመንታት የሚገለጥ፥ ግልጽ ትርጉም አንዲሰጥ ተደርጐ ያልተያያዘ የተደበላላቀ ነው፡፡ ከጉባዔ ፊት ቁመው ከማስተማራቸው በፊት አንብበው መተርጐም መቻል ይገባቸዋል፡፡GWAmh 44.1

  በትምህርት ቤታችን የሚገኙ መምህራን አጥንተው በደንብ ማስተማር አለባቸው፡፡ መምህራን ችሎታቸው ሳይፈተን ማስተማር መጀመር የለባቸውም፡፡ ወደ ወንጌል ሥራ ከመግባታቸው በፊት ልምድ ባላቸው መፈተን አለባቸው፡፡GWAmh 44.2

  በትምህርት ቤታችን የሚሰጠው ትምህርት በሌሎች ኮሌጆች ወይም የትምህርት መስጫዎች አንደሚሰጠው ትምህርት መሆን የለበትም፡፡ በዝቅተኛ ደረጃም መሰጠት የለበትም፡፡ የትምህርቱ ዋና ዓላማ ለታላቁ ለእግዚአብሔር ቀን የተዘጋጀ ሕዝብ ለማቅረብ መሆን አለበት፡፡ ተማሪዎቹ በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ ሊሰለጥኑ ይገባል፡፡ ትምህርት ቤቶቻችን ለሰማይ ገጣሚ የሚሆኑ ተማሪዎችን እንዲያስመርቁ ነው፡፡ ከዳኑት የሚስማሙ ይሆናሉ፡፡GWAmh 44.3

  ለአገልግሎት የስለጠኑት ሳይውሉ ሳያድሩ ቦታቸውን ይያዙ፡፡ ቤት ለቤት እየዞሩ መልዕክቱን የሚያዳርሱ ይፈለጋሉ፡፡ እግዚአብሔር ወንጌል ባልደረሳቸው ቦታዎች ብርቱ ጥረት አንዲደረግ ይፈልጋል፡፡ በሕዝብ ቤቶች ፀሎት፣ መዝሙርና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መደረግ አለበት:: ትፅዛዙ ሊፈጸም የሚገባው አሁን ነው፡፡ «ያዘዝኋችሁን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አስተምራቸው” (ማቴ. 28:20) ይህን ሥራ የሚያከናውኑ ሰዎች ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ዕውቀት ሊኖራቸው መከላከያቸው «ተጽፏል” የሚለው ሐረግ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ብርሃን የሰጠን ለሌሎች እንድናስተላልፍ ነው፡፡ በክርስቶስ የተነገረው ቃል የሰዎችን ልብ ይገባል፡፡ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚለውን ሐረግ ያዳመጠ ሁለ መልካም ፍሬ ያፈራል፡፡ ግን ታማኝ አገልጋይ የተገኘ እንደሆነ ነው::GWAmh 44.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents