Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የወጣቶች ክፍያ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

  ወጣቶች ልባቸውን ለእግዚአብሔር ሲሠጡ ኃላፊነታችን አበቃ ማለት አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ሥራ ተካፋይነት ተሰምቷቸው ሥራውን ለማራመድ ኃላፊነታቸውን መገንዘብ አለባቸው፡፡ የሥራውን ብዛትና መሥራት አንዳለባቸው ለወጣቶች ማስገንዘብ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ለጌታቸው እንዴት አንደሚሠሩ መማር አለባቸው፡፡ ነፍሳትን በአጥጋቢ ዘዴ ለክርስቶስ ለመመለስ መማር፣መሠልጠን እና መጋራት አለባቸው፡፡ ወጣት ጓደኞቻቸውን ለይምሰል ሳይሆን ከልብ መርዳት እንደሚገባቸው አስተምሯቸወ፡፡ ወጣቶች ተካፋይ የሚሆኑባቸው ልዩ ልዩ የሥራ መስኮች ይዘጋጁላቸው፡፡ ያን ጊዜ ለእግዚአብሔር መሥራት ይማራሉ፡፡ የወጣቶችን ስሜት በረዥም ስብከት አናነሳሳለን ብላችሁ አታስቡ፡፡ ሌላ በሥራ የሚገለጹ ማነቃቂያዎችን አቅዱ፡፡GWAmh 132.2

  በየሳምንቱ ወጣቶች ምን ሥራ እንደሞከሩና እንዴትስ እንደተሳካላቸው አንዲናገሩ ዕድል ይሰጣቸው፡፡ ስብሰባው እንዲህ ዓይነቶች አዲስ አጋጣሚዎች የሚሰማበት ከሆነ አሰልች ወይም አድካሚ አይሆንም::፡ አነቃቂ ይሆንና ተካፋዮቹ ይበረክታሉ፡፡GWAmh 132.3

  በሚገባ ተኮትኩቶ ያደገ የወጣቶች መክሊት በቤተ ክርስቲያናችን ወስጥ ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች በትኩሱ ጉልበታቸው ብዙ ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡ ይህ ብርታታቸው በሚገባ መንገድ ካልተመራ የራሳቸውን መንፈሳዊ ሕይወትና ጓደኞቻቸውን ለሚበድል መጥፎ ተግባር ያውሉታል፡፡GWAmh 132.4

  የመምህሩና የተማሪዎቹ ልቦች በፍቅር ይተሳሰሩ፡፡ ብዙ ፈተናዎች እንደሚያጋጥሟቸው አይረሳ፡፡ የወጣቶችን የበላይነት ስሜት ጠባይ አንዘነጋና በቢህ መጥፎ ስሜት አማካኝነት የሚመጣባቸውን ፈተና አናስተውልሳቸውም፡፡ ምክትል ጠባቂው በጎቹን እንዴት ሊጠብቃቸው አንደሚገባ በቸሩ አረኛ ምሣሌነት ተገልጦለታል፡፡GWAmh 133.1

  ጠባቂው በጎቹን ሲመራ በጎቹ ቀረብ ብለው ይከተሉታል፡ መራመድ የማይችልን የበግ ግልገል ታቅፎ ሲሄድ እናቲቱ በጎን በጎን ትከተለዋለች፡፡ ስለክርስቶስ ሥራ ኢሣይያስ እንዲህ ይላል ‹መንጋውን እንደ እረኛ : ጠቦቶቹንም በክንዱ ይሸከማል፡፡ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል፡፡› (አሳ. 40፡11) ጠቦቶች የዕለት ምግብ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በርህራሄና በትጋት ሁል ጊዜ ሊጠበቁ ይገባል:: ተለይተው ቢጠፉ ፈላጊ ያሻቸዋል፡፡ ከዚህ በላይ የተሰጠው መግለጫ በስዕል የተገለጠልኝ ሲሆን አገላለጡ ግሩም ነው:: ምክትል ጠባቂው አንደቸሩ ጠባቂ የሚመራቸውን መውደድ ይገባዋል፡፡GWAmh 133.2

  ወንጌላውያን ወንድሞቼ ሆይ፤ በአገልግሉታችሁ ለወጣቶች በራችሁን ክፈቱ፡፡ ፈተና ሲያጋፍጣቸው የግል ጥረታችሁ አይለያቸው፡፡ በየአቅጣጫው ክፉ እንዲሠሩ ይጋበዛሉ፡፡ አጃችሁን ከእነርሱ አታንሱ፡፡ ወደቤታችሁ ጋብዟቸው፡፡ በቤተሰብ ጸሎታችሁ ይካፈሉ፡፡ የሰማይን መንገድ ብሩህና ቅን ለማድረግ ክርስቶስ የጣለብንን አደራ አንዘንጋ፡፡GWAmh 133.3

  ወጣቶች እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ ካስተማርናቸው ለከፍተኛ አገልግሎት ተዘጋጁ ማለት ነው፡፡ በቀላል የትህትና አቀራረብ በሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳት ሊመለሱ ይሻሉ፡፡ በዓለም ፊት ታላላቅ ሊቃውንት ተብለው የሚቆጠሩት እግዚአብሔርን በሚወድ በመጠነኛ ሰው የፍቅር ንግግር ልባቸው ይነካል፡፡ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጆች ቃላት ለብዙ ጊዜ ታትሞ የኖረውን የሰዎችን ልብ ይከፍታል፡፡ ኢሣይያስ 40:11:GWAmh 133.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents