Go to full page →

ምዕራፍ ፳፪—በዓለም ውስጥ መሆን ግን የዓለም አለመሆን፡፡ CCh 157

ሕዝቡ የሆን የክርስቶስን አምሳያነት ከመምሰል ይልቅ ዓለምን የመምሰል አሥጊነታችን ታየኝ፡፡ እኛ አሁን በዘለዓለማዊ ዓለም ዳርቻዎች ላይ ነን ነገር ግን የጊዜውን ፍጻሜ እንድናርቅ ይመራን ዘንድ የነፍሳት ባለጋራ ሐሳብ ነው፡፡ ሰይጣን ያምላክ ትእዛዝ ጠባቂ ሕዝብ እንደሆኑ የሚናገሩትንና በሰማይ ደመና በኃይልና በታላቅ ክብር የመድኃኒታችንን ዳግመኛ መገለጽ እንጠብቃለን የሚሉትን ያምላክ ሕዝብ በማንኛውም በታሰበው አኳኋን አደጋ ይጥልባቸዋል፡፡ እነሱ ክፉውን ቀን እንዲያዘገዩና ልማዶቹን እየተከተሉ በመንፈስ እንደ ዓለም ይሆኑ ዘንድ በተቻለው ብዙዎችን ይመራል፡፡ እውነት እንዳላቸው ከፍ ያለ ስመ ክርስትናቸውን የሚነዙትን የብዙዎችን ልቦችና ሐሳቦች የዓለም መንፈስ ሲገዛቸው እንደነበረ ሳይ ድንጋጤ ተሰማን፡፡ ራስን መውደድና የራስ ፍትወት በነሱ ዘንድ የሚወደዱ ናቸው ነገር ግን እውነተኛ አምላኮትንና ዓይነተኛ ቅንነትን የሚሳተፉ አይደለም፡፡ 14T306; CCh 157.1