Go to full page →

በየሥፍራው የሚሆኑተን የቤተ ክርስቲያን አለቆች መምረጥና መሾም፡፡ CCh 110

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቲቶስ እንዲህ ሲል ይጽፋል ‹‹የጎደለውን ሁሉ ታቆም ዘንድ ቀሳውስትም ትሾም ዘንድ በያገሩ እዳዘዝሁህ፡ ሰውም ነውር የሌለበት ቢሆን፡፡ ያንዲት ምሸትም ባል ቢኖር ያመኑም ልጆቸ ቢሆኑለት በርኩሰት የማይኖሩ የማይታዘዙም አይደሉ፡፡ ለጳጳስ ይገባዋልና ነውር የሌለበት ይሆን ዘንድ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ፈቃዱን የማከተል የማይቆጣ የጸጅም ዘካሪ ያይደለ የማይማታም የረከሰውንም ረብ የማይሻ›› ቲቶስ ( (-(:: ‹‹በማንም ላይ ፈጥነህ እጅህን አትጫን›› ( ጢሞ :: CCh 110.3

በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያናት ሽማግሎችን የማቋቋምና የመሾም ሥራ ተቸኩሎበታል የመጽሐፍ ቅዱስ ደንብ ችላ ተብሏል ስለዚህ የሚያሳዝን መከራ በቤተ ክርስቲያን ላይ ደርሶባታል፡፡ ለኃላፊነት ሥራ በምንም ጎና ተገቢዎች ያልሆኑትን ሰዎች ለመሾም ማለት በማንኛውም ችሎታ ለእግዚአብሔር ጉዳይ ለማገልገል ከመቻላቸው በፊት መመለስ ከፍ ያሉ የተከበሩና ጥሩዎች ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በመሾም ረገድ መሪዎችን መምረጥ ላይ ይህን ያህል በጣም መቸኮል አይገባም፡፡ 105T617,6’8; CCh 110.4