«በእምነት ለተገዙለት መንግሥትን ሰጣቸው
ጽድቅን ለተላበሰውደግሞ ከድክመታቸው
አንስቶ ኃይል ሰጣቸው፡፡» EDA 160.1
ከትምህርት ሰጪነቱ አንፃር መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ከያዛቸው ታሪኮች የበለጠ ዋጋ ያለው ሌላ ክፍል የለም፡፡ እነዚህ ታሪካች ከሌሎች የሚለዩበት ዋናው ነገር በሕይወት የተከናወኑ ፍፁም እውነተኛ የሆኑ የሕይወት ታሪኮች በመሆናቸው ነው፡፡ ውስን የሆነ አእምሮ ያለው ማንኛውም ሰው የሌላውን ሰው ሥራዎች በሁሉም ነገሮች ያለው ማንኛውም ሰው የሌላውን ሰው ሥራዎች በሁሉም ነገሮች ትክክል መተርጐም አይችልም እርሱ ልብን ማንበብ የሚችለው ፍላጐትን ከተግባር ለይተው የሚያንቀሳቅሱትን ምንጮች ምስጢር ከሚያውቀው ከእርሱ በስተቀር የባሕሪይን ትክክለኛ ገጽታ በእውነት የሚገልጽ ወይም የሰውን ልጅ ሕይወት በአስተማማኝ ስዕል መግለጽ የሚችል ሌላ ማንም ሰው የለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ስዕላዊ መግለጫ የማገኘው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ EDA 160.2
መጽሐፍ ቅዱስ የምንሠራው ነገር የእኛ ማንነት ውጤት መሆኑን በግልጽ ከማስተማር በስተቀር ሌላ ዕውነት የለውም፡፡ የሕይወት ገጠመኞች በአመዛኙ የሐሳቦቻችንና የተግባሮቻችን ፍሬዎች ናቸው፡፡ EDA 160.3
«...ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም፡፡» ምሳ 26፡2 EDA 160.4
«የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁንም መልካም ይሆናልሃል በሉት እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ ክፉም ደርሶበታል፡፡» ኢሳ 3፡10፡11 EDA 161.1
«ምድር ሆይ ስሚ... የአሳባቸውን ፍሬ ክፉን ነገር አመጣባችኋለሁ፡፡» ኤር 6፡19 EDA 161.2
ይህ እውነታ በጣም ከባድ ነው፡፡ በጥልቀት መጠናትም አለበት፡፡ እያንዳንዱ ሥራ ተመልሶ በሠሪው ላይ ይመጣል፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሕይወቱን የተረገመ የሚያደርግ ክፉ ሥራ ውስጥ ከገባ ፍሬውን ከዘራው ዘር እንደሚያጭድ ሊገነዘብ ይችላል፡፡ እደዚያም ሆነን እንኳ እያለን ያለ ተስፋ አይደለንም፡፡ EDA 161.3
እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት የራሱ መሆኑ ተረጋግጦለት እያለ ያዕቆብ የልደት መብት ወይም ብኩርና ለማግኘት ሲል ተንኮል ሰራ፡፡ በወንድሙ ጥላቻ ምክንያትም የዘራውን አጨደ፡፡ በሃያ ዓመት ስደት ራሱ ወንጀል ተሠራበት እጅግ ቢያንስ ነፍሱን ለማዳን በስደት መንከራተት ነበረበት፡፡ ሁለተኛም ደግሞ እንደገና የሥራውን አገኘ፡፡ የራሱ ባህሪ ክፋት ዘር ፍሬ ሆኖ በልጆቹ ደረሰበት፡፡ ለሰው ልጅ ትክክለኛ ቅጣት መሠጠቱን የሚያሳይ እውነተኛ ስዕል ነው፡፡ EDA 161.4
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፡፡ «መንፈስም የፈጠርኩትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለመ አልጣላም፡፡ የፈጠርኩትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፡፡ ሁልጊዜም አልቆጣም፡፡ ስለኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቆጥቼ ቀሰፍሁት፣ፊቴን ሰውሬ ተቆጣሁ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ፡፡ መንገዱን አይቻለሁ፡፡ አፈውሰውማለሁ ለእርሱና ስለእርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ፡፡ የከንፈሮቹን ፍሬ እፈጥራለሁ በሩቅም በቅርብመ ላለው ሰላም ሰላም ይሁን ይላል እግዚአብሔር ፡፡» ኢሳ 57፡16-19 EDA 161.5
ያዕቆብ ሐዘንና ጭንቀት በተሞላበት ጊዜ ግራ ገብቶት አልቀረም፡፡ በወንድሙ ላይ በፈፀመው ስህተት አዝኖ በመፀፀት ተናዘዘ፡፡ ኤሳው እንደሚገድለው በቁጣ ሲዝትበት ከእግዚአብሔር እርዳታ ጠየቀ፡፡ «ከአምላክ ጋር ታገለ ከመለአኩም ታግሎ አሸነፈ አልቅሶም ለመነው፡፡» «እርሱም በዚያ ባረከው፡፡» ሆሴ 12፡4 ዘፍ 32፡29 ምህረት የተደረገለት ይህ ሰው በእርሱ በጌታ ታላቅ ኃይል ከዚያ በኋላ ተተኪ ወራሽ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ልዑል ሆነ፡፡ ከተናደደው ወንድሙ ቁጣ ብቻ ሳይሆን ራሱንም ከራሱ ጥፋት አዳነ፡፡ በውስጡ የነበረው የክፋት ኃይል ተሰበረ፡፡ ባሕሪይውም ተለወጠ፡፡ EDA 162.1
በምሽት ብርሃን ነበረ፡፡ያዕቆብ የሕይወት ታሪኩን መለስ ብሎ እየተመለከተ ሕይወትን የሚያቆየውን የእግዚአብሔርን ኃይል ተመለከተ፡፡ ‹ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ› ዘፍ 48፡16 አለ፡፡ EDA 162.2
የዚያው ዓይነት ገጠመኝ በያዕቆብ ልጆች ሕይወት ደግሞ ደረሰ፡፡ ኃጢአት ተገቢውን ቅጣት ሲያስከትል መናዘዝ ደግሞ ለሕይወት ጽድቅን ሲያመጣ በድጋሜ ተከስቷል፡፡ EDA 162.3
እግዚአብሔር ሕጐቹን የሚሠርዝ ወይም የሚያነሳ አይደለም፡፡ ሕጐቹን የሚቃረን ነገርም አይሠራም፡፡ የሀጢአት ሥራዎችን ግን እንዳልተደረጉ አድርጐ አይመልሳቸውም፡፡ ይለውጠዋል እንጅ፡፡ በፀጋው እርግማን እንኳ ቢሆን በረከትን ያመጣል፡፡ EDA 162.4
ከያዕቆብ ልጆች መካከል ሌዊ የተባለው እጅግ ጨካኝና መበቀልን የሚፈልግ የነበረና ሽቾማይቶችን በመግደል ረገድ ዋናው አታላይ የነበረ ነው፡፡ የሌዊ ባህሪይዎች በልጅ ልጆቹ ዘር ወርዶ ተንፀባረቀ፡፡ ከእግዚአብሔርም ይኸንን ትዕዛዝ አመጣባቸው «በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ፡፡» ዘፍ 49፡7 ነገር ግን መናዘዛቸው ለውጥ አመጣ፡፡ በሌላው በዙሪያቸው ከነበረው አመፀኛ ሕዝብ መካከል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው በመገኘታቸውም ርግማኑ ከፍተኛ የክብር ልዩ ምልክት ወደ መሆን ተለውጧል፡፡ EDA 162.5
«በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የሸከም ዘንድ እርሱንም ለማገልገል በፊቱ ይቆም ዘንድ በስሙም ይባረክ ዘንድ እግዚአብሔረ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ፡፡» «ቃል ኪዳ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፡፡ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፡፡ እርሱም ፈራኝ ከስሜም የተነሳ ደነገጠ፡፡... ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ ብዙ ሰዎችንም ከሀጢአት መለሰ፡፡› ዘዳግ 10፡8 ሚል 2፡5-6 EDA 163.1
የተመረጠው የመቅደሱ አገልጋይዎች የሆኑት ሌዋውያን የሚወረስ መሬት አልተሰጣቸውም ለእነሱ ተብሎ በተሠራው መንደር በአንድ ላይ ተቀመጡ፡፡ ለኑሮአቸው የሚሆነውን ነገር የሚገኙትም ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንዲሆን ከሚሰጠው የአሥራትና ልዩ ልዩ ስጦታዎች ገቢ ነው፡፡ የሕዝቡ አስተማሪዎች ነበሩ በየድግሡ ላይ ሁሉ እንግዶች ነበሩ፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይና ወኪሎቹ እንደመሆናቸው በየሄዱበት ይከበሩ ነበር፡፡ አጠቃላይ ወኪሎቹ እንደመሆናቸው በየሄዱበት ይከበሩ ነበር፡፡አጠቃላይ ለሕዝቡ የተሰጠው ትዕዛዝ ‹በምድርህ ላይ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ፡፡› ‹እግዚአብሔር የሌዊን ነገድ ለየ፡...ከወንድሞቹ ጋር ርስትና ክፍል የለውም፡፡ እግዚአብሔር ርስቱ ነው፡፡› የሚል ነው፡፡ ዘዳ 12፡19 ምዕ 10፡9 EDA 163.2