ሰው «በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና» ምሳ 23፡7 የሚለው በትክክል እውነት ነው፡፡ ይህም በእስራኤላዊያን ሕይወት ውስጥ ሌላ ቦታ ላይ መግለጫ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በከነአን ድንበር ላይ ሰላዬቹ አገሪቱን ሲመረምሩ ቆይተው ሲመለሱ ስለሁኔታው መግለጫ አቀረቡ፡፡ ሀገሪቱን እንዴት አድርገው ለመያዝ እንደሚችሉ በመፈራታቸው የመሬቷን ውበትና የሞላባትንም ፍራፍሬ ማየት አልቻሉም፡፡ የከተሞች ሰማይ ደረስ በግንብ መታጠር ግዙፍ ተዋጊ ወታደሮች የብረት ሠረገላዎች ተስፋ አስቆረጣቸው፡፡ እግዚአብሔርን ከጥያቄ ውጪ አድርገው ተውትና ተጠራጣሪዎቹን ሰላዮቻቸውን አምነው ሕዝቡ በአድነት እንዲህ በማለት ጮኸ፡፡ «በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ፡፡» ዘሁ 13፡31 ቃላቸውም እውነት ሆነ፡፡ በአነዚያ ላይ መውጣት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ሕይወታቸውን በበረሃ ጨረሱ፡፡ EDA 164.1
ሀገሪቱ ውስጥ ገብተው ስለላ ካደረጉት ሰዎች መካከል ሁለቱ ነገሩ ተቃወሙ፡፡ «እኛ ከእነሱ እንበለጣለን እናሸንፋቸዋለንም አሉ፡፡» ዘሁ 13፡30 የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ከእነኛ ግዙፎች በግንብ ከታጠሩ ከተሞችና ከብረት ሠረገላዎች የበለጠ ኃያል መሆኑን አሥረዱ፡፡ ለእነሱ ለራሳቸው የተናገሩት ቃል ትክክል ነበር፡፡ ምንም እንኳን የአርባ ዓመቱን የበረሃ ጉዞ ከወንድሞቻቸው ጋር መጋራት ቢኖርባቸውም ካሌብና እያሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር ገቡ፡፡ ከግብጽ ሲወጣ የነበረውን የጌታ ሠራዊት ልብ ድፍረት እንደያዘ ካሌብ የእነኛ ግዙፍ ወታደሮች ከነአናዊያንን አባርሮ አስወጣቸው፡፡ የወይን ቦታዎችና መጥመቂያዎች እግሮቹ የደረሰበት ቦታ ሁሉ የእርሱ ይዞታ ሆነ፡፡ የሸሹና የተቃወሙ ሁሉ በበረሃው ውስጥ ጠፍተው በቀሩም እንኳ የእምነት ሰዎች ደግሞ ደግሞ ከኤሾል የወይን ፍሬ ተመገቡ፡፡ EDA 164.2
መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ ብቻ እንኳ ከእውነት መንገድ መውጣት የሚያስከትለውን አደጋ ስህተቱን በፈፀመውና ከእርሱመ ጋር በነገሩ ለተባበሩ በሙሉ የሚያስከትለውን አደጋ በግልጽ ብርሃን ከማስቀመጥ የበለጠ ሌላ እውነት አይገልጽም፡፡ EDA 165.1
በዓለማችን ላይ እጅግ ከባዱ ለማስተካከል የሚያስቸግር የክፋት ምሽግ በማይመለስ ልቅ ኃጢአተኛ ወይም ተወግዞ በተገለለው ጥፋተኛ ሕይወት ውስጥ ያለው ሳይሆን በተቃራኒው ድንቅ የተከበረና ምስጉን መስሎ በሚታየው ለአንድ ኃጢአት ሲል አንድ ክፋት የሚሠራው ሰው ነው፡፡ በምስጢር ከአንድ ግዙፍ ፈተና ጋር የምትታገል ነፍስ በገደል አፋፍ ላይ እየተንቀጠቀጠች ባለች ሕይወት የሚመስለው ኃጢአት ለመስራት የምትሞክር ነፍስ የሚደርስባት መንገላታት ነው፡፡ በሕይወቱ ውስጥ ከፍተኛ የእውነትንና የክብርን ጽንሰ-ሐሳቦችን የማስተዋል ስጦታ ያለው ሰው ከእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ አንዷን ሐሳብ እያወቀ ከተላለፈ ክቡር ችሎታዎቹን ለሀጢአት ፍላጐት ሆን ብሎ ለውጧል ማለት ነው፡፡ የአእምሮ ድንቅ ችሎታ ልዩ ክህሎት፣ርህራሄ የልግሥናና የደገነት ሥራዎች እንኳ ነፍሶች በጥፋት ሀሳብ ላይ እንዲነሱ የሚገፋፋ የሰይጣን አደጋዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ EDA 165.2
እግዚአብሔር የአንዷን የኃጢአት ሥራ ውጤት ሳይቀር ብዙ ምሳሌዎችን የሚሰጠን ለዚህ ነው፡፡ ከሚያሳዝነው ከዚያ በአንዲት ኃጢአት ምክንያት ብቻ ከመጣብን ‹ሞትን እና ዋይታን በዓለም ላይ ያመጣና ኤደንንም ያሳጣን› ለሰላሳ ብሮች ሲል የክብር ጌታን እስከሸጠው ሰው ታሪክ ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በእነዚህ ምሳሌዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ ከዋናው የሕይወት መንገድ ወጥተን ወደጐን እንዳንሄድ እንደማስጠንቀቂያ መብራት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ EDA 165.3
ወደ ሰብዓዊ ፍጡር ድክመቶችና ስህተቶች እምነትን የመልቀቅ ፍሬ ወደ ሆነው ስህተት አንድ ጊዜ እንኳን ማዘንበል የሚያስከትለው ውጤት እናስታውስ ዘንድ ሌላ ማስጠንቀቂያ አለ፡፡ EDA 166.1
ከእምነቱ አንዲት ነገር ብቻ በማጉደሉ፤ ኤልያስ የሕይወት ሥራው በአጭሩ አቋረጠ፡፡ በመላው እስራኤል ፋንታ ተተክቶ የወደቀበት ሽክም እጅግ ከባድ ነበር፡፡ ለገር አቀፍ የነበረውን የጣኦት አምልኮ በማውገዝ የሰጣቸው ማስጠንቀቂያዎች ታማኝነት የተሞላባቸው ነበሩ፡፡ በነዚያ ሦስት ዓመት ተኩል የረሀብ ዘመናት የመናዘዝ ወይም ንስሀ የመግባት አንድ ዓይነት ምልክት ለማየት ሲጠብቅ ቆየ፡፡ በእምነትም ኃይል የጦኦት አምልኮ ወዲያ ተጣለ፡፡ የተባረከው ዝናብም ቆይቶ በእስራኤል ላይ እንደሚወርድ ለሚጠበቀው የበረከት ካፊያ ማስረጃ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ከኢዛቤል ዛቻ የተነሳ በፍርሀትና በጭንቀት በርሮ ወደ በረሃ ሄደና በተደበቀበት ቦታ ይሞት ዘንድ ፀለየ፡፡እምነቱ ጠፋ ወደቀ፡፡ እሱ የጀመረውን ሥራ እሱ እንዲጨርሰው አልሆነም፡፡ እግዚአብሔር እሱን የሚተካ ሌላ ሰው መርጦ እንዲቀባ አዘዘው፡፡ EDA 166.2
ነገር ግን እግዚአብሔር አገልጋዩ ያበረከተውን ልባዊ ግልጋሎት መዝግቦት ነበር፡፡ ስለዚህም ኤልያስ በበረሃ ውስጥ ተስፋ በመቁረጥና በብቸኝነት ጠፍቶ እንዲቀር አልተደረገም፡፡ ምድረበዳው የእሱ የመቃብር ቦታ እንዲሆ አይደለም የእግዚአብሔር መላዕክት ወደ እርሱ ክብር የሚዘልቁበት ስፍራ እንጅ፡፡ EDA 166.3
እነዚህ የሕይወት ታሪኮች እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር አንድ ቀን ምንነታቸውን የሚያስተውልበትን፣ ኃጢአት እፍረትንና ጥፋትን ብቻ እንደሚያመጣ፣ አለማመን ማለት ውድቀት መሆኑን የእግዚአብሔር ምህረት ግን እጅግ የመጨረሻ ጥልቅ በሆነው ቦታው እንደሚደርስ እምነት ደግሞ ንስሀ የገባችን ነፍስ ወደ ላይ እንደምታነሳና የእግዚአብሔር ልጆች የሚኖሩበትን እንደምታጋራ ይገልፃሉ፡፡ EDA 167.1