Go to full page →

“ጤናማ፣ ፍሬ የሚያፈራ ቅርንጫፍ አድርገኝ” Amh2SM 237

ቀኑ ሰኔ 29 ቀን 1892 ዓ.ም ነበር፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ ጸሎቴ፣ ኢየሱስ ዛሬ ልጅህን ጠብቅ የሚል ነበር፡፡ በጥበቃህ ሥር አድርገኝ፡፡ በሕያው ግንድ ላይ ያለ ጤናማ፣ ፍሬ የሚያፈራ ቅርንጫፍ አድርገኝ፡፡ ክርስቶስ «ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም” ብሏል (ዮሐ. 15፡ 5)፡፡ በክርስቶስ ውስጥ ሆነን በእርሱ አማካይነት ሁሉን ማድረግ እንችላለን፡፡ Amh2SM 237.4

መላእክት የሚሰግዱለት፣ የሰማያዊ ኳየርን ዝማሬ የሰማ፣ በዚህች ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ የልጅነት እሮሮአቸውን ለመስማት ዝግጁ በመሆኑ የልጆች ሀዘን ነክቶታል፡፡ ብዙ ጊዜ ሀዘናቸውን ጸጥ በሚያደርጉና በሚያስረሱ ርህራሄ በተሞሉ ቃላቶቹ እያሳሳቃቸው እንባዎቻቸውን ጠርጎላቸዋል፡፡ በኢየሱስ ጥምቀት ጊዜ በርግብ መልክ በእርሱ ላይ ያንዣበበው ምሳሌ የሚወክለው የባሕርይ ገራምነትን ነው፡፡ --Manuscript 19, 1892. Amh2SM 238.1