Go to full page →

«እጄ በመሪው ላይ ነው» Amh2SM 391

የጌታ መምጫ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ ወደ እኛ ቀርቧል፡፡ ታላቁ ተጋድሎ ወደ ፍጻሜው መቃረቡ እንዴት አስደናቂ ነገር ነው! በፍጻሜው ሥራ ውስጥ የሚያገኙንን ችግሮች እንዴት መያዝ እንዳለብን አሁን ማወቅ አንችልም፤ ነገር ግን ሶስቱ ታላላቅ የሰማይ ኃይሎች ሥራ ላይ መሆናቸውን፣ መለኮታዊው እጅ በመሪው ላይ መሆኑን እና እግዚአብሔር ሥራውን ከፍጻሜ እንደሚያደርስ አንርሳ፡፡ በጽድቅ የሚያገለግለውን ሕዝብ ከዓለም ይሰበስባል፡፡ Amh2SM 391.3

በጌታ ሥራ ውስጥ ኃላፊነትን የሚሸከሙትን ሰዎች አስፈሪ የሆኑ መከራዎች ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል፡፡ እነዚህን መከራዎች ሳስብ ያንቀጠቅጠኛል፡፡ ነገር ግን «እጄ በመሪው ላይ ስለሆነ በራሴ መንገድ መለኮታዊውን እቅድ እፈጽመዋለሁ” የሚል ቃል ይመጣል፡፡ The Review and Herald May 5, 1903. Amh2SM 391.4