Go to full page →

ቋሚ የመጽሔት ደምበኞች ማፍራት ChSAmh 208

መጽሔቶቻችንንና ጋዜጦቻችንን በደንበኝነት በየአድራሻቸው እንዲላክላቸው ቅድሚያ የስድስት ወር ወይም የአንድ ዓመት ክፍያ የሚከፍሉ ደምበኞችን በማፍራት ብርሐንን ወደ ብዙዎች አእምሮ ለማድረስ በሚደረገው እንቅስቃሴ እህቶቻችን ውጤታማ ሥራ መሥራት ይችላሉ፡፡Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 208.1

ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን እውነትን ለማሰራጨት የሚያስችሉን ሁናቴዎች ቢመቻቹልንም ነገር ግን ሕዝባችን በእነዚህ መልካም አጋጣሚዎች እየተጠቀመ አይደለም፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑ ያሉ ምዕመናን መክሊቶቻቸውን ተጠቅመው ነፍሳትን የማዳንን አስፈላጊነት አይመለከቱም -አይሰማቸውምም፡፡ የጤና መልእክቶቻችንን ጨምሮ መጽሔቶቻችንን በደምበኝነት ተመዝግበው የሚያገኙ አንባቢያንን የመፈለጉን ኃላፊነት አልተረዱም፡፡ ይህ ዘርፍ መጻሕፍቶቻችንንና በራሪ ጽሑፎቻችንን ለሌሎች የማስተዋወቅ ሥራን ያካትታል፡፡-Testimonies, vol. 4, p. 391. ChSAmh 208.2