ሐዘን፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የተዳከመ እምነትና መታመን በብዘዎች ይስተዋላል፡፡ በእነዚህ ሁናቴዎች ውስጥ የሚገኙ ነፍሳት እነርሱ ከሚገኙበት በከፋ እጦት ያሉ ወገኖችን ሲረዱ እግዚአብሔር ያበረታቸዋል፡፡ መጻሕፍቶቻችንን በመሸጥ መልካም ሥራ ውስጥ ይታቀፉ፡፡ በዚህ አገልግሎት ሌሎችን መርዳት ከመቻላቸው በተጨማሪ በሥራው በሚያገኙት ተሞhሮ የአምላካዊው ተልዕኮ ተባባሪ እጅ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ያገኛሉ፡፡ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ በቃተቱ ቁጥር ብርሐን ለማግኘት አጥብቀው ወደሚሹ ወገኖች ይልካቸዋል፡፡ ክርስቶስ ከአጠገባቸው ሆኖ ምን ማለትና ማድረግ እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል፡፡ ሌሎችን በማጽናናታቸው እነርሱ ራሳቸው መጽናናት ያገኛሉ፡፡--The Colporteur Evangelist, p. 40. ChSAmh 208.3