Go to full page →

ታካችነትና ችላ ባይነት ChSAmh 277

ብርሐናችን ወደ ሌሎች ሕዝቦች ወጥቶ እንዳያበራእግዚአብሔር የተወልንን ሥራ ከመሥራት ያıደን እንደ ሐዝብ በስንፍና የተሞላ ቸልተኝነትና በጥፋተኝነት የሚያስጠይቅ አለማመን ይታይብናል፡፡Life Sketches of Ellen G. White, p. 213. ChSAmh 277.3

እንደ ሕዝብ ብርሐናችንን ወደ ሌሎች አገሮች የማሰራጨት ኃላፊነታችንን ችላ ያልን መሆኑን ጌታ አሳይቶኛል፡Life Sketches of Ellen G. White, p. 212. ChSAmh 277.4

በመለኮታዊው ጣልቃ ገብነት የሚከፈቱልንን በሮች እየተራመድንባቸው አይደለም፡፡ የሱስና መላእክቱ በሥራ ላይ ናቸው፡፡ እግሮቻችን ወደ ፊት መራመድ ተስኖአቸው ወደ ኋላ ብንቀርም አምላካዊው ሥራ ግን ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚከፍትልንን በሮች የምንከታተል ከሆነ እያንዳንዱን ክፍተት በቀላሉ ለይተን በመመልከት ብርሐን ተስፋፍቶ ወደ ሌሎች አገሮች እንዲሰራጭ በሚያስችለው በዙሪያችን በሚገኝ እያንዳንዱ ነገር የበለጠ ተጠቃሚ እንሆናለን፡፡Life Sketches of Ellen G. White, p. 212, 213. ChSAmh 277.5