ሰይጣን በብርቱ ኃይል መሰበክ ከሚኖርበት ከሦስቱ መላእከት መልእክት ሰዎችን ለመነጠል ጫና እያደረገና የማሳት ኃይሉን እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ ጌታ ሐዝቡን እየባረከና የጠላትን ማሳቻዎች ለይተው እንዲያውቁ እያዘጋጃቸው መሆኑን ሰይጣን ሲመለከት--በአንድ ጽንፍ ወግ አጥባቂነትን በሌላው ደግሞ ቀዝቃዛ ኃይማኖታዊ መልh እንዲመጣ ልዩ ችሎታውን ተጠቅሞ ከእጁ ሊያስገባቸው ይሠራል፡፡ ነቅተን የምንመለከትበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሰይጣን ወደ እኛ መሃል የሚያደርገውን የመጀመሪያውን እርምጃ በንቃት እንከታተል፡፡-Review and Herald, Jan. 24, 1893. ChSAmh 53.2
በቤተ ክርስቲያኖቻችን የከፉ ኢ-ግብረገባዊ ተግባራት ይስተዋላሉ፡፡ በዓለም ላይ ማብራት ያልቻሉ ኃይማኖታዊ መልክ ብቻ የተላባሱ አያሌ የታይታ ሰዎች አሉ፡፡-Review and Herald, March 24, 1891. ChSAmh 53.3