Go to full page →

ምዕራፍ 4—ክርስቲያኑ አገልጋይ የሚጋፈጣቸው የዓለም ሁናቴዎች ChSAmh 68

በዓለም የሚተወነው ድራማ ChSAmh 68

ዓለም የቴአትር መድረh እንደመሆኗ ነዋሪዎቿ በመጨረሻው የምድር ታሪክ መደምደሚያ ላይ የየራሳቸውን ክፍል ለመተወን በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡ ሰዎች ራስ ወዳዱን ዓላማ ለማስፈጸም ካልሆነ በቀር ሁሉ አቀፍ ኅብረት ሊመሰርቱ አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር እየሆነ ያለውን ሁሉ እየተመለከተ ነው፡፡ አመጻን ለመረጡት ፍጡራን የታቀደው አምላካዊ ዓላማ የታለመለትን ግብ ይመታል፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ይህ ሁሉ መደናገር፣ ትርምስና ምስቅልቅል ለጊዜው ምድርን እንዲያላጋት ቢፈቅድም ነገር ግን በሰው ልጆች እጅ ተላልፋ አልተሰጠችም፡፡ ሰይጣን በክርስቶስ ተመስሎ ጽድቅ የጎደለውን የመጨረሻውን የማሳሳቻ ትዕይንት ለመተወን እንዲገለጥ የሚያስችል ራሱን ከምስጢራዊ ማኅበረሰቦች ጋር በአንድ አስተሳስሮ በመሥራት ላይ የሚገኝ ኃይል አለ፡፡ ለተባበረው ኃይል ውጤታማነት በብርቱ ስሜት እየሠሩ የሚገኙ ኃይላት የጠላትን ዕቅድ በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ የአንድ ነገር መነሻ የራሱ የሆነ የሚያስከትለው ውጤት ይኖረዋል፡፡Testimonies, vol. 8, pp. 27, 28. ChSAmh 68.1