Go to full page →

ምን መከሰት ይችል ነበር! ChSAmh 118

እያንዳንዱ የክርስቶስ ወታደር የግል ድርሻውን ቢወጣና እያንዳንዱ የጽዮን ግንብ ጠባቂ የመለከት ድምጽ ቢያሰማ ምድር የማስጠንቀቂያውን መልእክት በሰማች ነበር፡፡ ሆኖም ሥራው በብዙ ዓመታት ወደ ኋላ ቀርቶአል፡፡ ሰዎች ባንቀላፉበት ወቅት ሰይጣን ግስጋሴአቸውን ሰርቋል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 29. ChSAmh 118.3

ወንዶችና ሴቶች የተጋረጠብንን አደጋ አስተውለንና ከእንቅልፋችን ነቅተን መልእክቱን በማወጅ የተመደበልንን ሥራ እንሥራ፡፡ እያንዳንዱ ሰባተኛ ቀን አድቤንቲስት የተጣለበትን የግል ኃላፊነት ቢወጣ ኖሮ የአባላት ብዛት ዛሬ ከሚስተዋለው በእጅጉ በላቀ ነበር፡፡ በመላው የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የእግዚአብሔርን ሕግ የመታዘዝ መልእክት አክብረው የተቀበሉ በኖሩ ነበር፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 25. ChSAmh 119.1

የምኅረትን መልእክት ለዓለም የመስጠቱ አምላካዊ ዓላማ በሕዝቡ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ ዳግም ተገልጦ ጻድቃን በእግዚአብሔር ከተማ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በተደረገላቸው ነበር፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 450. ChSAmh 119.2