Go to full page →

መንፈሳዊ ልፍስፍስነት ChSAmh 147

ልምምድን ተከትሎ _ ብርታትና _ ጥንካሬ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተሰጥኦ የሚጠቀሙ ሁሉ ለአገልግሎቱ ሊያውሉ የሚችሉት ላቅ ያለ ችሎታ አላቸው፡፡ ለአምላካዊው አገልግሎት አንዳችም ድርሻ የማያበረክቱ በጸጋም ሆነ በእውነት ዕውቀት ከማደግ ይገታሉ፡፡ ያለ ሥራ ከመቀመጥ ውጪ እጅና እግሮቹን ለማንቀሳቀስ ፈቃደኛ የማይሆን ሰው ውሎ አድሮ ሊጠቀምበት ይችል የነበረውን ጉልበት ያጣል፡፡ በዚህ የተነሳ ክርስቲያኑ ሥራ ላይ እንዲያውለው በእግዚአብሔር የተሰጠውን ጉልበት ጥቅም ላይ ባለማዋሉ በክርስቶስ እንዳያድግ መገታት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የነበረውንም ተሰጥኦ የመጠቀም ኃይል በማጣት የመንፈሳዊ ልፍስፍስነት ተጠቂ ይሆናል፡፡ ለእግዚአብሔርና ለባልንጀራቸው ፍቅር ያላቸው፣ በዐለቱ ላይ የተመሰረቱ፣ የጠነከሩና በእውነት ላይ ተደላድለው የተቀመጡ፤ ሌሎችን ለመርዳት ብርቱ ትግልና ጥረት ያደርጋሉ፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን በስሜት ተገፋፍቶ ለአንድ ቀን ወይም ለአንድ ወር አይሠራም፡፡ ይልቁንም አምላካዊውን መርኅ መሰረት አድርጎ ሕይወቱን ሙሉ እግዚአብሔርን ያገለግላል፡፡Testimonies, vol. 5, p. 393. ChSAmh 147.1