Go to full page →

የጤና ቅድስና MYPAmh 154

ሰይጣን ልክ ወደ ክርስቶስ እንደመጣ ሁሉ ከፈተናዎቹ ጋር በብርሐን መልአክ ተመስሎ ወደ ሰዎች ይመጣል፡፡ ሰውን በፈተናዎቹ ለማሸነፍና ሕይወቱን በማጥፋት ድል ለመቀዳጀት እንዲያስችለው በአካልና በሞራል የደከመ እንዲሆን ለማድረግ ሲሰራ ነበር፡፡ በዚህም ሰው ውጤቱን ሳያገናዝብ በምግብ ፈተና እንዲሸነፍ በማድረግ ተሳክቶለታል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠውን የአካልና የአእምሮ ኃይላትን ካዳከመ በኋላ ሰው እግዚአብሔር የሚጠብቅበትን ኃላፊነቶች በትክክል መፈጸም እንደማይችል ሰይጣን በደንብ ያውቃል፡፡ አእምሮ የአካል መዲና ነው፡፡ መሻትን ካለመግዛት የተነሣ ነገሮችን የሚያገናዝቡ ክፍሎች ሲደነዝዙ ዘላለማዊ ነገሮችን መለየት አይችልም፡፡ MYPAmh 154.1