Go to full page →

ክፍል 8—የአምልኮ ሕይወት MYPAmh 161

ቅዱስና የሚያስተምር የእግዚአብሔር መንፈስ በቃሉ ውስጥ አለ፡፡ ከእያንዳንዱ ገጽ ብርሐን፣ አዲስየከበረ ብርሐን ይበራል፡፡ እዚያ እውነት ተገልፆአል፤ ቃላቶችና ዓረፍተ ነገሮች የእግዚአብሔር ድምጽ ለነፍስ በሚናገር መልክ ብሩህና ለጊዜው ገጣሚ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ MYPAmh 161.1

የእግዚአብሔር መንፈስ ለወጣቶች ለመናገርና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ሐብትና ውበት ሊገልጥላቸው ይወዳል፡፡ በታላቁ መምህር የተነገሩ ተስፋዎች ስሜትን ይይዙና ነፍስን መለኮታዊ በሆነው ኃይል ህያው ያደርጋሉ፡፡ ፍሬያማ በሆነ አእምሮ ውስጥ ለፈተና እንደ መከላከያ አጥር የሚያገለግል ከመለኮታዊ ነገሮች ጋር ትውውቅ ያድጋል፡፡ Christs Object Lessons, P.132. MYPAmh 161.2