Go to full page →

ኃይማኖትና ጤና MYPAmh 159

«የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡» መጥፎ ልምዶችና ኃጢአተኛ ልምምድ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ለመለኮታዊ የእውነት ኃይል ሲያስገዙ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሕይወታቸው በመግባት ተራ ለሆኑ ሰዎች ብርሃንና ማስተዋልን ይሰጣቸዋል፡፡ እውነት በልብ ውስጥ ይተገበራል፤ ሽባ የሆነ ይመስል የነበረው የግብረገብ ኃይል ይነቃቃል፡፡ ተቀባዩ ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ ጠንካራና የጠራ ማስተዋል ይኖረዋል፡፡ ነፍሱን ዘላለማዊ ከሆነው አለት ጋር አጣብቋል፡፡ በክርስቶስ ከመሆኑ የተነሣ በሚያሰማው የደህንነት ስሜት ምክንያት ጤና ይሻሻላል፡፡ በመሆኑም ኃይማኖትና የጤና ሕጎች እጅ ለእጅ ተያይዘው ይሄዳሉ፡፡ Testimonies for the Church, vol. 4, P. 553-55. MYPAmh 159.5