Go to full page →

እንዴት መጸለይ እንዳለብን MYPAmh 162

ነገር ግን ጸሎት ሊስተዋል በሚገባ ሁኔታ አልተስተዋለም፡፡ የጸሎቶቻችን ዓላማ እግዚአብሔር የማያውቀውን አንድ ነገር ለእርሱ ለማሳወቅ አይደለም፡፡ ጌታ እያንዳንዱን የነፍስ ምስጢር ያውቃል፡፡ ጸሎቶቻችንን ረዥምና ከፍ ባለ ድምፅ የሚጸለዩ ማድረግ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሔር የተደበቁ ሐሳቦችን ያውቃል፡፡ በምስጢር ስንጸልይ በምስጢር የሚያይ አምላክ ጸሎታችንን ይሰማና በግልጽ ዋጋውን ይሰጣል፡፡ MYPAmh 162.2

ጉስቁልነታችን በፍጹም ሳይሰማን ጉስቁልነታችንን ለእግዚአብሔር ለመንገር የሚጸለዩ ፀሎቶች የግብዝነት ፀሎቶች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የሚሰማው ጸሎት ኃጢአተኛነታችን ተሰምቶን የምንጸልየው ጸሎት ነው፡፡ «ታላቅና ከፍ ብሎ ያለው ለዘላለም የሚኖር፣ ስሙም ቅዱስ የሆነ እንዲህ ይላል፡- እኔ ከፍ ባለው በተቀደሰ ስፍራ እኖራለሁ፡፡ እንደዚሁም ለኃጢአቱ ከሚያዝንና ትሁት መንፈስ ካለው ጋር የየዋሃንን መንፈስ ለማነቃቃትና ለኃጢአታቸው የሚያዝኑትን ልብ ለማንቃት አብሬ እሆናለሁ፡፡» MYPAmh 162.3

ፀሎት በእግዚአብሔር ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ ለማምጣት የታቀደ አይደለም፤ እኛን ከእርሱ ጋር ስምሙ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ፀሎት የተግባር ቦታን አይወስድም፡፡ ከልብ የተፀለየና ቶሎ ቶሎ የተደረገ ፀሎት በእግዚአብሔር ፊት የአሥራት ምትክ ሆኖ ተቀባይነትን አያገኝም፡፡ ፀሎት ለእግዚአብሔር ያሉንን ዕዳዎች አይከፍልልንም…፡፡ MYPAmh 162.4