Go to full page →

ፀሎት ኃይል ያመጣል MYPAmh 162

ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ የምናገኘው ብርታት ለዕለቱ ተግባሮቻችን ያዘጋጀናል፡፡ በየዕለቱ የሚገጥሙን ፈተናዎች ፀሎት የግድ እንዲያስፈልገን ያደርጋሉ፡፡ በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ከፈተናዎቹ መጠበቅ እንድንችል የአእምሮ ፍላጎቶቻችን ያለማቋረጥ በፀጥታ ፀሎት ወደ ላይ መውጣት አለባቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ሊለዩን በተሰሉ ሁኔታዎች ዙሪያችን ሲከበብ ለእርዳታና ለጥንካሬ ያለን አቋማችን መድከም የለበትም፡፡ እንደዚህ ካልሆነ በስተቀር ትዕቢትን መስበርና ከአዳኛችን የሚያርቁንን የኃጢአት ተግባራት ማሸነፍ አንችልም፡፡ የእውነት ብርሃን ሕይወትን በመቀደስ ተቀባዩን ለማሸነፍ እየጣሩ ያሉትን የልቡን የኃጢአት ስሜቶች ለይቶ እንዲያውቅ በማድረግ በክርስቶስ ሥራ ሰይጣንን ለመቋቋም እያንዳንዱን ነርቭ እንዲያሰራና ያሉትን ኃይሎች በሙሉ ተግባር ላይ እንዲያውል አስፈላጊ ይሆናል፡፡ The Youth’s Instructor, August 18, 1898. MYPAmh 162.5