Go to full page →

በእውቀት ማደግ MYPAmh 166

ለወጣቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስን ግለጡላቸው፣ ትኩረታቸውን ወደ ተደበቁ ሐብቶች ሳቡ፣ የእውነትን እንቁዎች እንዲፈልጉ አስተምሩአቸው፡፡ ይህም ፍልስፍና በውስጡ አቅፎ የያዘው ነገር ሁሉ ሊሰጥ የማይችለውን የአእምሮ ብርታት ይሰጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚዳስሳቸው ዋና ጉዳዮች፣ በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተነገሩ ተራ ቃላቶች ክብር ያላቸው መሆናቸው፣ ለአእምሮ የሚሰጣቸው ከፍ ያሉ ጉዳዮች፣ ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚመጣው ኃይለኛና የጠራ ብርሃን ማስተዋልን ብሩህ በማድረግ ለመገንዘብ እስከማይቻልና በፍጹም ሙሉ በሙሉ ማብራራት እስከማይቻል ድረስ የአእምሮ ኃይሎችን ያሳድጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለሐሳቦቻችን ወሰን የለሽ መስክን ያቀርባል፡፡ ያውም ካልተቀደሰ አእምሮ ከሚፈልቁ ጥልቀት የሌላቸው ፈጠራዎች በባሕርዩ እጅግ የበለጠና የከበረ ሲሆን ልዩነቱም ሰማያት ከምድር የሚርቁትን ያህል የራቀ ነው፡፡ በእግዚአብሔር መገለጥ የተፃፈ የሰው ዘር ታሪክ በእያንዳንዱ ሰው እጅ ገብቷል፡፡ ሁሉም የየራሳቸውን ምርመራ ማድረግ መጀመር ይችላሉ፡፡ ከመጀመሪያ ወላጆቻችን ጋር በኤድን በተቀደሰ የዋህነት፣ ከእግዚአብሔርና ኃጢአት ከሌላቸው መላእክት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቆሙበት ቦታ መተዋወቅ ይችላሉ፡፡ ከዚያም እንዴት ኃጢአት ወደ ዓለም እንደገባና በሰብዓዊ ዘር ላይ ያስከተለውን ውጤት ደረጃ በደረጃ የተቀደሰ ታሪክን በመከተል የሰውን አለመታዘዝ፣ አለመናዘዝና የኃጢአትን ቅጣት ማየት ይችላሉ፡፡ MYPAmh 166.5