Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእውቀት ማደግ

    ለወጣቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስን ግለጡላቸው፣ ትኩረታቸውን ወደ ተደበቁ ሐብቶች ሳቡ፣ የእውነትን እንቁዎች እንዲፈልጉ አስተምሩአቸው፡፡ ይህም ፍልስፍና በውስጡ አቅፎ የያዘው ነገር ሁሉ ሊሰጥ የማይችለውን የአእምሮ ብርታት ይሰጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚዳስሳቸው ዋና ጉዳዮች፣ በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተነገሩ ተራ ቃላቶች ክብር ያላቸው መሆናቸው፣ ለአእምሮ የሚሰጣቸው ከፍ ያሉ ጉዳዮች፣ ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚመጣው ኃይለኛና የጠራ ብርሃን ማስተዋልን ብሩህ በማድረግ ለመገንዘብ እስከማይቻልና በፍጹም ሙሉ በሙሉ ማብራራት እስከማይቻል ድረስ የአእምሮ ኃይሎችን ያሳድጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለሐሳቦቻችን ወሰን የለሽ መስክን ያቀርባል፡፡ ያውም ካልተቀደሰ አእምሮ ከሚፈልቁ ጥልቀት የሌላቸው ፈጠራዎች በባሕርዩ እጅግ የበለጠና የከበረ ሲሆን ልዩነቱም ሰማያት ከምድር የሚርቁትን ያህል የራቀ ነው፡፡ በእግዚአብሔር መገለጥ የተፃፈ የሰው ዘር ታሪክ በእያንዳንዱ ሰው እጅ ገብቷል፡፡ ሁሉም የየራሳቸውን ምርመራ ማድረግ መጀመር ይችላሉ፡፡ ከመጀመሪያ ወላጆቻችን ጋር በኤድን በተቀደሰ የዋህነት፣ ከእግዚአብሔርና ኃጢአት ከሌላቸው መላእክት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቆሙበት ቦታ መተዋወቅ ይችላሉ፡፡ ከዚያም እንዴት ኃጢአት ወደ ዓለም እንደገባና በሰብዓዊ ዘር ላይ ያስከተለውን ውጤት ደረጃ በደረጃ የተቀደሰ ታሪክን በመከተል የሰውን አለመታዘዝ፣ አለመናዘዝና የኃጢአትን ቅጣት ማየት ይችላሉ፡፡MYPAmh 166.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents