Go to full page →

መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ሽልማት MYPAmh 172

እውነትን መሻት ፈላጊውን በእያንዳንዱ ቦታ ይሸልመውና እያንዳንዱ አዲስ ግኝት ሌላ የበለፀገ የምርምር መስክ ይከፍትለታል። ሰዎች በአእምሮአቸው በሚያሰላስሉት ነገር ይለወጣሉ። ተራ የሆኑ ሐሳቦችና ጉዳዮች ትኩረትን ከሳቡ ግለሰቡ በተራ ቦታ ይሆናል። ጥልቀት በሌለው የቃሉ ማስተዋል በመርካት ሊያገኝ የሚገባውን ነገር ችላ የሚል ከሆነ እግዚአብሔር ሊሰጠው የሚሻውን የበለፀገ በረከት ማግኘት አይችልም:: የሰው አእምሮ በጣም ከተለማመዳቸው ነገሮች አንፃር መስፋት ወይም መጥበብ የአእምሮ ህግ ነው። MYPAmh 172.1

የአእምሮ ኃይሎች ትጋትና ቀጣይነት ባለው እውነትን የመመርመር ሥራ ውስጥ ካልገቡ በስተቀር በእርግጠኝነት እየጠበቡ ይሄዱና የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቅ ትርጉም የማስተዋል ችሎታቸውን ያጣሉ። አእምሮ ጥቅስን ከጥቅስ ጋርና መንፈሳዊ ነገርን ከመንፈሳዊ ነገር ጋር በማነፃፀር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በመመርመር ሥራ ላይ ከዋለ ይሰፋል። ብልሃተኛና ትጉህ ለሆነ ተማሪ የበለፀጉ የአስተሳሰብ ሃብቶች ተዘጋጅተው እየጠበቁ ናቸው። Review and Herald, July 17, 1888. MYPAmh 172.2