Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ሽልማት

    እውነትን መሻት ፈላጊውን በእያንዳንዱ ቦታ ይሸልመውና እያንዳንዱ አዲስ ግኝት ሌላ የበለፀገ የምርምር መስክ ይከፍትለታል። ሰዎች በአእምሮአቸው በሚያሰላስሉት ነገር ይለወጣሉ። ተራ የሆኑ ሐሳቦችና ጉዳዮች ትኩረትን ከሳቡ ግለሰቡ በተራ ቦታ ይሆናል። ጥልቀት በሌለው የቃሉ ማስተዋል በመርካት ሊያገኝ የሚገባውን ነገር ችላ የሚል ከሆነ እግዚአብሔር ሊሰጠው የሚሻውን የበለፀገ በረከት ማግኘት አይችልም:: የሰው አእምሮ በጣም ከተለማመዳቸው ነገሮች አንፃር መስፋት ወይም መጥበብ የአእምሮ ህግ ነው። MYPAmh 172.1

    የአእምሮ ኃይሎች ትጋትና ቀጣይነት ባለው እውነትን የመመርመር ሥራ ውስጥ ካልገቡ በስተቀር በእርግጠኝነት እየጠበቡ ይሄዱና የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቅ ትርጉም የማስተዋል ችሎታቸውን ያጣሉ። አእምሮ ጥቅስን ከጥቅስ ጋርና መንፈሳዊ ነገርን ከመንፈሳዊ ነገር ጋር በማነፃፀር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በመመርመር ሥራ ላይ ከዋለ ይሰፋል። ብልሃተኛና ትጉህ ለሆነ ተማሪ የበለፀጉ የአስተሳሰብ ሃብቶች ተዘጋጅተው እየጠበቁ ናቸው። Review and Herald, July 17, 1888.MYPAmh 172.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents