Go to full page →

የሰይጣንን የአስማት ኃይል መስበር MYPAmh 181

የጥንቆላ መጻሕፍት መቃጠል አለባቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ። በሰይጣን ምኩራብ ውስጥ ፍትወትን ለማነሳሳትና ለመፈፀም የተዘጋጁ ማራኪ ቦታዎች አሉ። ነገር ግን በዚያ ቦታ ምስክር አለ! ያ በዓይን የማይታይ ጎብኚ በጨለማ ለተፈፀሙ ተግባራት ምስክርነት ይሰጣል። በከንቱዎች፣ ኩሩዎችና ደስታ ፈላጊዎች ማህበር ውስጥ መሪው ሰይጣን ስለሆነ በዚያ የደስታ ስሜት ውስጥ ዋናው አንቀሳቃሽ እርሱ ነው። እርሱ በዚያ ቦታ በድብቅ ይገኛል። የጥንቆላ ስራ በሁሉም አቅጣጫ በዙሪያችን ነው! ዓለምም ሆነ ቤተክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማድረግ አልመውት የማያውቁትን ነገር እንዲያደርጉ ሊመራቸው በሚችል ኃይል ተፅእኖ ስር ናቸው። ሊፈጽሙት ያለው ነገር ቀደም ብሎ ተነግሮአቸው ቢሆን ኖሮ ነብዩ ለሐዛኤል ስለ ወደ ፊት ሕይወቱ በነገረው ጊዜ እንደተደነቀ እነርሱም ይደነቁ ነበር። MYPAmh 181.5

በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ስር ያልሆነው እያንዳንዱ ወንድ፣ ሴትና ህጻን በሰይጣን የጥንቆላ ተፅእኖ ስር ነው፣ በመሆኑም በንግግሩም ሆነ በሕይወት ምሳሌነቱ ሌሎችን ከእውነት መንገድ እንዲርቁ ይመራቸዋል። የክርስቶስ የሚለውጥ ፀጋ በልብ ውስጥ ሲሆን ኃጢአተኛው ለብዙ ጊዜያቶች እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ታላቅ መዳን ችላ ብሎ በመቆየቱ ነፍስ በቅዱስ ቁጣ ትሞላላች። ያኔ እራሱን፣ አካሉን፣ ነፍሱንና መንፈሱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ይሰጥና ከእግዚአብሔር በተሰጠው ፀጋ ከሰይጣን ጓደኝነት ይለያል። እርሱም እንደ ኤፌሶን ሰዎች ጥንቆላን በመካድ ከሰይጣን ጋር የሚያስተሳስረውን የመጨረሻ ክር ይቆርጣል። የጨለማውን ልዑል ባንዲራ በመተው በደም በተቀለመው በልዑል አማኑኤል ባንዲራ ስር ይሆናል። የጥንቆላ መጻሕፍትን ያቃጥላል። Youth’s Instructor, Nov. 16,1883. MYPAmh 181.6