Go to full page →

ሙዚቃ ለመልካም ነገር •ኃይል MYPAmh 192

ሙዚቃን ለመልካም ነገር ታላቅ ኃይል ማድረግ ይቻላል! ነገር ግን ከዚህ የአምልኮ ዘርፍ መጠቀም የሚገባንን ያህል አልተጠቀምንም። በአጠቃላይ ሰዎች መዝሙር የሚዘምሩት በስሜት በመነሳሳት ወይም ለተለዩ ሁኔታዎች እንዲገጥም በማድረግ ነው። በሌላ ጊዜያቶች ደግሞ የሚዘምሩ ሰዎች እንዲዘባራርቁ ይተውና ሙዚቃው በቦታው ባሉት ሰዎች አእምሮ ሊያመጣ የሚገባውን ውጤት ሳያመጣ ይቀራል። ሙዚቃ ውበት፣ ልብን መግራትና ኃይል ሊኖረው ይገባል። ድምፆች በምስጋናና በአምልኮ ዝማሬዎች ይሰሙ። ሊተገበር የሚችል ከሆነ በሙዚቃ መሣሪያ በመታገዝ ግርማ ያለው ዝማሬ ተቀባይነት ያለው ቁርባን ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ይውጣ። Testimonies for the church, Vol. 4, P 71 MYPAmh 192.2