Go to full page →

የመስዋእትነት ሽልማት MYPAmh 195

ሌሎችን ለመባረክ ጥቅም ላይ የዋለ ንብረት አፀፋውን ይመልሳል። በትክክል ስራ ላይ የዋለ ሀብት ታላቅ መልካም ተግባር ይፈጽማል:: ነፍሳት ወደ ክርስቶስ ሊመለሱበት ይችላሉ። የክርስቶስን የሕይወት ዕቅድ የሚከተል ሰው በእግዚአብሔር አደባባዮች ጌታ የደከመላቸውንና በምድር ላይ መስዋዕት የሆነላቸውን ነፍሳት ያያል። የዳኑት ለእነርሱ መዳን ምክንያት የሆኑትን ሰዎች በአመስጋኝነት መንፈስ ያስታውሷቸዋል። ነፍሳትን በማዳን ስራ ታማኝ ለነበሩ ሰዎች ሰማይ እጅግ የከበረ ይሆንላቸዋል። Christ’s Object Lessons,P.373 MYPAmh 195.6