Go to full page →

ያለምክንያት መሆን MYPAmh 198

እያንዳንዱ ሰው በአካል በሰራው መጠን በሚፈረድበት በዚያ ቀን ዛሬ አስራትና ሥጦታዎችን ላለመስጠት ራስ-ወዳድነት የሚያቀርባቸው ሰበቦች ጤዛ በፀሐይ ፊት እንሚቀልጥ ይቀልጣሉ። ጊዜው ለዘላለም ባያልፍባቸው ኖሮ ስንቶች ሄደው እንደገና ባሕርያቸውን ለመገንባት በተደሰቱ ነበር! ነገር ግን እግዚአብሔርን በየሳምንቱ፣ በየወሩና በየአመቱ እየዘረፉ የቆዩ ሰዎችን መዝገብ ለመለወጥ ጊዜው ያልፋል…። MYPAmh 198.6

እራስ ወዳድነት ክፉ ገዳይ ነው። ራስ ወዳድነትና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለተገቡ ስምምነቶች የሚታዩ ግድ የለሽነቶች፣ እንደ እርሱ ታማኝ መንጋዎች ለመስራት እምቢተኝነት ማሳየት በአድራጊዎቹ ላይ እርሱ አስቀድሞ እንደተናገረው •ርግማን አምጥቶባቸዋል። እነዚህ ነፍሳት እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ለይተዋል! በቃላቸውና በምሳሌነታቸውም ሌሎች በእግዚአብሔር ግልፅ ትዕዛዛት ላይ እምነት •እንዲያጡ መርተዋቸዋል። በመሆኑም •እርሱ በነዚህ ሰዎች ላይ በረከቱን ማውረድ አልቻለም። MYPAmh 199.1