Go to full page →

የግል ኃላፊነት MYPAmh 200

ሰማያዊ አባታችን እንድንሰራ ከሰጠን ችሎታ የበለጠም ሆነ ያነሰ አይፈልግብንም። በባሪያዎቹ ላይ ሊሸከሙት የማይችሉትን ሸክም አይጭንባቸውም። “ፍጥረታችንን ያውቀዋል! አፈር እንደሆንንም ያስታውሳል።” እርሱ ከእኛ የሚፈልግብንን ሁሉ በመለኮታዊ ፀጋ ማድረግ እንችላለን። MYPAmh 200.1

“ከእያንዳንዱ ሰው በተሰጠው መጠን ያንኑ ያህል ይፈለግበታል::” አንድን ነገር ለማድረግ ካለን ችሎታ አንዲት ነጥብ እንኳን ብናሳንስ በየግላችን ተጠያቂ እንሆናለን። ለአገልግሎት ያለንን እያንዳንዱን አጋጣሚ ጌታ ያለመሳሳት ይመዝነዋል። ጥቅም ላይ ያልዋሉ ችሎታዎች ልክ እንደተሻሻሉ ችሎታዎች ሁሉ ከግምት ውስጥ ይገባሉ። መክሊቶቻችንን በትክክል ተጠቅመን መሆን እንችል ለነበረውና ላልሆንነው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ተጠያቂ ያደርገናል:: የሚፈረድብን ማድረግ እያለብን ያሉንን ኃይሎች ለጌታ ክብር ባለመጠቀማችን ሳንፈጽም በቀረነው መሰረት ነው። ምንም እንኳን ነፍሳችንን ባናጣም ሳንጠቀምባቸው የቀረናቸው መክሊቶችን ውጤት በዘላለማዊነት ውስጥ እንገነዘባለን:: ልናገኝ እንችል ለነበረውና ሳናገኝ ለቀረነው እውቀትና ችሎታ ሁሉ ዘላለማዊ ጥፋት ይኖራል። MYPAmh 200.2

ነገር ግን ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ብንሰጥና በሥራችን የእርሱን መመሪያዎች ብንከተል ለስራው ተፈፃሚነት ጌታ ኃላፊነቱን ይወስዳል። በታማኝነት የምናሳየው ጥረት ለሚያስገኘው ክንውን እርሱ ግምታዊ ሃሳብ አያቀርብም:: ስለ አለመሳካት አንድ ጊዜ እንኳን ማሰብ የለብንም:: መተባበር ያለብን ውድቀትን ከማያውቀው ከእርሱ ጋር ነው። MYPAmh 200.3

ስለ ራሳችን ድካምና አለመቻል መናገር የለብንም። ይህንን ማድረግ ግልፅ የሆነ በእግዚአብሔር አለመታመንና ቃሉን መካድ ነው። ከሸክሞቻችን የተነሳ ስናጉረመርም ወይም እንድንሸከማቸው የጠራንን ኃላፊነቶች ለመሸከም እንቢ ስንል እርሱ እንድንሰራ ኃይል ሳይሰጠን እንድንሰራ የሚፈልግብን ጨካኝ ጌታ ነው እያልን ነን። Christ’s object Lessons P. 362-363. MYPAmh 200.4