Go to full page →

የገንዘብ ጥቅም MYPAmh 200

ገንዘባችን የተሰጠን እራሳችንን እንድናከብርና ከፍ ከፍ እንድናደርግ አይደለም። እንደ ታማኝ መጋቢዎች ለእግዚአብሔር ክብር መጠቀም አለብን። አንዳንዶች ከሀብታቸው የተወሰነውን ብቻ የእግዚአብሔር እንደሆነ ያስባሉ። ያንን የተወሰነውን ያህል ለኃይማኖታዊና ለበጎ አድራጎት ተግባራት ካስቀመጡ የቀራውን የራሳቸው ስለሆነ እንደፈለጉ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይቆጥሩታል። በዚህ ረገድ ስህተት እየፈፀሙ ናቸው። ያለን ሁሉ የጌታ ስለሆነ ስለ አጠቃቀማችን ተጠያቂዎች እንሆናለን። እያንዳንዷን ሳንቲም የምንጠቀምበት አጠቃቀም ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን እንደምንወድና ጎረቤታችንን እንደራሳችን እንደምንወድ ወይም እንደማንወድ ያሳያል። MYPAmh 200.5

ገንዘብ ታላቅ የሆነ መልካም ስራ ስለሚሰራ ታላቅ ዋጋ አለው። በእግዚአብሔር ልጆች እጅ ያለ ገንዘብ ለረሃብተኞች ምግብ ፣ ለተጠሙት መጠጥ፣ ለተራቆቱት ልብስ፣ ለተጨቆኑት መከላከያና ለታመሙት መርጃ ነው። ነገር ግን ገንዘብ ሌሎችን በመባረክና የክርስቶስ ስራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ለማድረግ ስራ ላይ ሳይውል ለሕይወት የሚያሰፈልጉ ነገሮችን ብቻ ለማሟላት ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ከአሸዋ የተሻለ ዋጋ የለውም ። Christ’s object Lessons P. 351. MYPAmh 200.6