Go to full page →

ራስን የማስደሰት ክፋቶች MYPAmh 201

ገና ለዓለም አዳኝ ልደት መታሰቢያነት የሚከበር በዓል መሆኑን እናስታውስ። ይህ ቀን በአጠቃላይ በግብዣና ያለ መጠን በመብላት ያልፋል። በማያስፈልግ የራስ ማስደሰቻ ላይ ብዙ ገንዘብ ይወጣል። የአካል፣ የአእምሮና የግብረ ገብ ኃይላትን መስዋዕት በማድረግ የምግብ ፍላጎትንና ስሜትን ማርኪያ ተግባራት ይፈፀማሉ። ይህም ልምድ ሆኗል። በእርግጠኝነት ማንንም የማይጠቅም ነገር ግን እግዚአብሔርን በሚያሳዝን ሁኔታ የንብረታችንን መኮብለል የሚያስከትል ኩራት፣ ፋሽንና ጉሮሮን ማርካት እጅግ ብዙ ገንዘብን ውጦታል። እነዚህ ቀናት እግዚአብሔርን ከማስደሰት ይልቅ ራስን በማስደሰት ያልፋሉ። ጤንነት መስዋዕት ተደርጓል፣ ገንዘብ ከመወርወር በከፋ ሁኔታ ባክኗል፣ ብዙዎች ያለ መጠን በመብላት ወይንም በሚያዋርድ ስካር ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ በዚህ መንገድ ነፍሳት ጠፍተዋል። MYPAmh 201.2

የእግዚአብሔር ልጆች ቀላል በሆነ አመጋገብ የሚደሰቱ ቢሆኑና የተሰጣቸውን ንብረት ብዙም ይሁን ጥቂት በስህተት ጨለማ ውስጥ ላሉ ነፍሳት ብርሃንን ለመላክ ጥቅም ላይ ቢያውሉ ኖሮ እግዚአብሔር ይከበር ነበር። የባልቴቶችና የወላጅ አልባ ልጆች ልብ የእነርሱን ምቾት በሚጨምሩና ረሃባቸውን በሚያስታግሱ በነዚህ ሥጦታዎች ምክንያት እንዲደሰት ማድረግ ይቻላል። MYPAmh 201.3