Go to full page →

የበዓል ቀናት ሥጦታዎች MYPAmh 201

የዓመት በዓላት እየተቃረቡ ናቸው። ይህንን በተመለከተ በየዓመቱ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሥጦታዎችን በመስጠት ምን ያህል ገንዘብ ወጪ እንደሚሆን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት መልካም ነው። በባህል ውስጥ ያሉ ልማዶች እጅግ ጠንካራ ከመሆናቸው የተነሣ በእነዚህ የበዓል ጊዜያቶች ለጓደኞቻችን ስጦታዎችን መከልከል እነርሱን ችላ ማለት ይመስላል። ነገር ግን ርህሩህ ሰማያዊ ለጋሽ አምላካችን ከነዚህ ምድራዊ ጓደኞቻቸን እጅግ አስበልጦ እንደሚፈልግብን ማስታወስ አለብን። ቀጥለው በሚመጡ የዓመት በዓል ጊዜያቶች ሥጦታዎቻችንን ለእግዚአብሔር አንሰጥምን? በዚህ ሥራ ህፃናትም መሳተፍ ይችላሉ። ለሚያስፈልጋቸው ድሆች አልባሳትና ጠቃሚ የሆኑ ቁሳቁሶች ሊሰጡ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ ለጌታ ሥራ ሊሰራ ይችላል። MYPAmh 201.1