Go to full page →

ራስን መካድ እግዚአብሔርን ያስደስተዋል MYPAmh 202

ራስን መካድን ተማርና ለልጆችህም አስተምራቸው። አሁን ሊሰራ ባለው ሥራ ውስጥ ራስን በመካድ የሚቆጠብ ገንዘብ ይፈለጋል። እየተሠቃዩ ያሉ እረፍት ሊያገኙ፣ የተራቆቱ ሊለብሱ፣ የተራቡ ሊመገቡ ይገባል። የወቅቱ እውነት ለማያውቁ ሰዎች መነገር አለበት…። MYPAmh 202.6

እኛ የክርስቶስ ምስክሮች ስለሆንን እግዚአብሔር አስቀድመው መምጣት አለባቸው ላላቸው ነገሮች ጆሮአችንን እንዳንሰጥ ጊዜያችንንና ትኩረታችንን ዓለማዊ ፍላጎቶች እንዲይዙ መፍቀድ የለብንም። በአጠገባችን ከፍ ያሉ ፍላጎቶች አሉ። “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም እሹ።” ክርስቶስ ሊፈጽመው ለመጣው ነገር ያለውን ሁሉ ሰጠ። የእርሱ ቃላት ለእኛም “ማንም ሊከተለኝ የሚፈልግ ቢኖር ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ይሸከምና ይከተለኝ” ይላሉ፡፡ “እናንተ ደቀመዘሙርቴ ትሆናላችሁ” ይሉናል:: ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈፀም በፈቃደኝነትና በደስታ ራሱን ሰጠ። ለሞት ያውም ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆነ። ራሳችንን መካድ እንደ ችግር ይሰማን ይሆን? የእርሱ ሞት ያለንንና ራሳችንንም ለእርሱ ሥራ ቀድሰን እንድንሰጥ እያንዳንዱን የእኛነታችንን ክፍል ሊያነሳሳ ይገባ ነበር። እርሱ ያደረገልንን ስናስብ ልባችን በፍቅር መሞላት አለበት። MYPAmh 202.7

እውነትን የሚያውቁ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የታዘዘውን ራስን መካድን ሲለማመዱ መልዕክቱ በኃይል ይሄዳል። ለነፍሳት መለወጥ የምንፀልየውን ፀሎት ጌታ ይሰማል። የእግዚአብሔር ህዝቦች ብርሃናቸው እንዲበራ ያደርጉና የማያምኑ ሰዎች የእነርሱን መልካም ሥራ በማየት ሰማያዊ አባታችንን ያከብራሉ። Review and Herald, Dec.,1, 1910. MYPAmh 203.1