Go to full page →

ብልጠት መንፈሳዊነት አይደለም MYPAmh 35

በሚገናኙአቸው ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትንና አድናቆትን እንዲያገኙ የሚያደርግ የሆነ ዓይነት ብልሃት ያላቸው ወጣቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ችሎታቸው የተቀደሰ አይደለም፡፡ በፀጋና በፈተናዎች ልምምድ ያልጠነከረና ያልፀና ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰብዓዊነት ጥቅምም ሆነ ለእርሱ ክብር ሊጠቀም አይችልም፡፡ በአምልኮ ሽፋን የእነርሱ ኃይሎች መጥፎ መስፈርቶችን ለመስራት ጥቅም ላይ ይውሉና ያልተለወጠ ልብ ያላቸው ሌሎች ሰዎች የእነርሱን ድርጊት ለመጥፎ ድርጊታቸው እንደ ሰበብ እንዲጠቀሙ ያደርጋሉ፡፡ ሰይጣን ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ብልጠት ተብሎ በሚጠራው በማይረባ ነገራቸው እንዲያዝናኑአቸው ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ እነርሱ የሚፈፅሙት ነገር ጠቃሚነታቸውን ዝቅ የሚያደርግ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ስራውን እንዲሰሩለት ባህሪያቶቻቸውን በሚመራና በሚቀርጽ በፈታኙ ቁጥጥር ስር ስላሉ ነው፡፡ችሎታ አላቸው፤ ነገር ግን ችሎታቸው ያልተገራ ነው፡፡ አቅሙ አላቸው፤ ነገር ግን እንዲሻሻል እድል ያልተሰጠው ነው፡፡ መክሊቶች ተሰጥተዋቸው ነበር፤ ነገር ግን በሞኝነታቸው ያለ አግባብ በመጠቀማቸውና ዝቅ በማድረጋቸው ሌሎችንም ወደ ራሳቸው ዝቅ ያለ ደረጃ ይጎትቱአቸዋል፡፡ MYPAmh 35.1

ክርስቶስ ራስን በመካድና መሥዋዕት በማድረግ፣ ውርደትን በመቀበል፣ ስድብንና ሐፍረትን በመቀበል ለነፍሶቻቸው ካሳ ከፍሎላቸዋል፡፡ ይህንን ያደረገው ከኃጢአት ባርነትና እነርሱን ለሌሎች ነፍሳት ጥፋት እስከተጠቀመ ድረስ ብቻ ግድ ከሚለው ጌታ ባርነት ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ነገር ግን በእነርሱ በኩል የአዳኙን ፍቅር ጥቅም እንደ ሌለው ስለሚያዩ አዳኙ ሥራቸውን የሚመለከተው በሃዘኔታ ነው፡፡ MYPAmh 35.2

እንደዚህ ዓይነቶቹን ወጣቶች የሚገጥማቸው ዘላለማዊ ጥፋት ነው፡፡ የምድር ሁሉ ፈራጅ የሆነው ለያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው በሚከፍልበት ቀን የእነርሱ ቧልትና ፌዝ ምን ይመስል ይሆን? ለመሠረት ሥራው ያመጡት እንጨት፤ገለባና ድርቆሽ ስለ ሆነ የሕይወት ዘመን ሥራቸው በሙሉ ይቃጠላል፡፡ እንዴት ያለ ኪሳራ ነው! MYPAmh 35.3

አገልግሎታቸውን ኢየሱስ እንዲያረጋግጥላቸው ወደ እርሱ በመመልከት፣ በየዕለቱ በመመዝገቢያ መጽሐፋቸው የየዕለቱን ስህተታቸውን እና ጥፋታቸውን፣ ሐዘናቸውን፣ በፈተና ላይ ያገኙትን ድሎቻቸውን፣ በክርስቶስ ያገኙትን ደስታና ሰላም በመጻፍ በእግዚአብሔር አገልግሎት ድርሻቸውን የሚወጡ ሰዎች ሁኔታ ምን ያህል የተሻለ ይሆን! እንደዚህ ዓይነት ወጣቶች የሕይወታቸውን መዝገብ የሚገያኙት በውርደትና ተስፋ በመቁረጥ አይደለም፡፡” The Youth’s Instructor, June 22, 1899. MYPAmh 35.4