Go to full page →

የተመረጡ ወኪሎች MYPAmh 35

የእርሱን ታማኝነት መመስከራችን ክርስቶስን ለዓለም ለማሳየት የሰማይ ምርጥ ዘዴ ነው፡፡ ፀጋውን በጥንቱ ቅዱሳን እንደተገለፀ አምነን መቀበል አለብን፡፡ ነገር ግን ከሁሉም የበለጠ ውጤታማ ዘዴ የራሳችን ልምምድ ምስክርነት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስክሮች መሆን የምንችለው የመለኮታዊውን ኃይል ስራ በህይወታችን ስንገልፅ ነው፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌሎች የተለየ ሕይወት እንዳለው ሁሉ የሕይወት ልምምዱም እንዲዚሁ ልዩ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚሻው ምስጋናችን የልዩነታችንን ምልክት እንደያዘ ወደርሱ እንዲወጣ ነው፡፡ Ministry of Healing, P.100. MYPAmh 35.5