Go to full page →

ኃይማኖት በቤት ውስጥ MYPAmh 212

ኃይማኖት በቤት ውስጥ እጅግ ያስፈልጋል። ስለዚህ በቤት ውስጥ የምንጠቀማቸው ቃላቶች ትክክለኛ ባሕርይ ያላቸው መሆን አለባቸው! አለበለዚያ በቤተክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው ምስክርነት ምንም ዋጋ አይኖረውም። ገርነትን፣ ደግነትንና ትህትናን በቤታችሁ ውስጥ ካላሳያችሁ በስተቀር እምነታችሁ ከንቱ ይሆናል። እውነተኛ የሆነ የቤት ኃይማኖት በብዛት ቢታይ ኖሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ኃይል ይኖር ነበር። MYPAmh 212.1