Go to full page →

ቤት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት MYPAmh 213

ወጣቶች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ቀድሰው በመስጠታቸው ደካማ አእምሮ ያላቸው ወይም ብቃት የሌላቸው አይሆኑም። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። ታላቁን ደህንነት ችላ ከሚል ግን እጅግ መክሊት ካለውና ከተማረ ሰው ይልቅ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ትንሽ ህፃን በእርሱ ዓይን ታላቅ ነው። ልባቸውንና ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የሚቀድሱ ወጣቶች በዚህ ድርጊታቸው የጥበብና ልቆ የመገኘት ምንጭ ከሆነው ጋር ራሳቸውን እያገናኙ ነው። MYPAmh 213.1